ለፌዴሬሽን የተዘጋጀ ስለ ፍተሻ እና ማስተካከያ ሥራዎች ማብራሪያ
ይህ ሰነድ ስለፍተሻ ሂደት ደረጃዎችና ኅዳር ላይ ስለሚከናወነው ስለማስተካከያ ሥራዎች ልየታ የሚገልጽ ነው፡፡
ፍተሻ ችግሮችን ለመለየት ጥሩ ነው ነገር ግን መፍትሔዎችን አያመላክትም/አያሳይም፡፡
ኃላፊነት፡-ይህ ሥራ የሚሠራው በውሃ ተጠሪ እና በወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ ድጋፍ ነው፡፡
የማስተካከያ ሥራዎች የሚባሉት፡- ማስተካከያዎች ሆነው በፍተሻ ሠዓት የተለዩ ችግሮችን ለማስተካከል የሚተገበሩ ሥራዎች ናቸው፡፡ ማስተካከያ ሥራዎች ሊባሉ የሚችሉ፡-
ያልተቀበረ/ያልተሸፈነ ቧንቧ ካለ = ካብ መካብ እና አፍር መመለስ
ቦኖው ጭቃማ/በጭቃ የተበላሸ ከሆነ = ዕለታዊ የጽዳት ሥራ ማደራጀት
ኃላፊነት፡- በውሃ ተጠሪው በተለዩ ችግሮች መነሻነት የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ የማስተካከያ ሥራዎችን በፎርማቱን ይሞላል
የኔትወርክ ፍተሻ ከውሃ ማህበራት ጋር በጋራ በመሆን የቧንቧ መስመሩን በመከተል እና በመፈተሽ እንዲሁም ሁሉንም የተቋማት ክፍሎችን በመፈተሽ ከምንጭ እስከ ቦኖ ድረስ መሆን አለበት፡፡
የቧንቧ መስመሩን ሳይፈትሹ የተቋሙን ዋና ክፍሎች ብቻ መፈተሽ እውነተኛ ፍተሻ ሊሆን አይችልም እንዲሁም ለኔትወርኩ ብልሽት ዋና ዋና ዋና የሚሆኑ ችግሮችን ለመለየት አያስችልም፡፡(ገላጣ የሆነ ቧንቧ፣መንገድ እና ገደል መሻገሪያዎችን)
ለምሳሌ፡- ምንጩ የተያዘበት ተፋሰስ አካባቢ የመከላከል ሥራ በተመለከተ:-ይህንን ጉዳይ ማወቅ የሚቻለው ከምንጩ ላይ በኩል/ራስጌ ሄዶ በማየት ብቻ ነው፡፡
በፍተሻ መዝገቡ ላይ ያለውን የፍተሻ ቼክሊስት መስመር በመስመር የውሃ ተጠሪው ድምጹን ከፍ አድርጎ በሚያነብበት ጊዜ የውሃ ማህበራቱ በማድመጥ ችግሩን በአካል በመገኘት እና በማየት ይሳተፋሉ፡፡ ከውሃ ተጠሪው ጋር ቡድኑ ቼክሊስቱ ሲነበብ ምንም ችግር ያለመኖሩን ከተስማማ √ ያደርጋል. ነገር ግን ትንሽ ችግር ያለ እንደሆነ X ያደርጋል.
ችግር ያለው ከሆነ (X) የውሃ ተጠሪው ቡድኑን ተከታዩን ጥያቄዎች መጠየቅ ይኖርበታል:-
የውሃ ተጠሪው የወረዳ ማኔጅመንት ኮሚቴ(ወማኮ) በተገኙበት ለፌዴሬሽኑ የማስተካከያ ሥራዎችን በዝርዝር ማሳወቅ
ይህን ሰነድ በመፈረም ሁሉም አባላቱ ስለሚከተሉት ጉዳዮች ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል: