የፍተሻ መነሻ ፣ የማስተካከያ እርምጃዎች እና ተሳትፎ
Initial Diagnostic, Corrective Measures & Engagement
ይህ ሰነድ የጥገና አጀማመርን፣እያንዳንዱን የአተገባበር ሂደትን፣ለጥገናው ኃለፊነት የሚወስደውን አካል፣ለጥገናው መሟለት ያለበትን ሰነድ እና የድጋፍ ዘዴው እንዴት መተግበር እንዳለበት ያስቀምጣል፡፡
ቁልፍ ትርጉም
1.1 ፍተሸ
የውሃ ተቋማትን ችግር/እንከን መለየት፣የውሃ ተቋማትን ደህንነት ሁኔታ እና ሁለንተናዊ ቁመና ለመፈተሽ የተዘጋጀ ቼክሊስት በመጠቀም የተቋሙን ችግር/እንከን መለየትና ቅጹን(ቼክሊስቱን) መሙላት። ይህ የፍተሻ ሥራ የሚጠናቀቀው በየዓመቱ በጥቅምት ወር ሲሆን ለተቋሙ የሚያስፈልገውን(ለዘላቂና አስተማማኝ የውሃ አገልግሎት) የማስተካከያ ሥራ የሚታወቀው /የሚገለጸው ፍተሻውን መሠረት አድርጎ ነው፡፡
1.2 የማስተካከያ ሥራዎች
በፍተሻው ደረጃ ላይ የተገለጹትን ችግሮች ለመፍታት መከናወን ያለባቸው ሥረዎች ናቸው፡፡
የማስተካከያ ሥራዎች የሚከተሉትን ሊሆኑ ይችላሉ፡-
ለምሳሌ ያልተቀበረ እና የተጋለጠ ቧንቧ መስመር ማስተካከያ ሥራ = ቧንቧ የተጋለጠበት ቦታ ላይ ካብ መገንባት እና አፈር ማልበስ
ለምሳሌ ችግር፡የውሃ ቦኖውና አካባቢው በጣም ቆሽሾ ተገኝቷል፡፡ ማስተካከያ ሥራ = የቦኖ ዕለታዊ ጽዳት ማድረግ
1.3 የደረጃ አሰጣጥ
የደረጃ አሰጠጥ አጠቃላይ የፍተሻ ውጤት ማሳያ ሆኖ በቀላሉ በደሽቦርድ የሚገለጽ እና ለወ/ው/ጽ/ቤት በሪፖርት የሚገለጽ ነው፡፡
የደረጃ አሰጣጡ ሥርዓት ከዚህ እንደሚከተለው በዝርዝር ቀርቧል፡፡
1.4 ሥልጠና
የሥልጠናው ሥርዓት ለአጠቃላይ ጥገናው ሂደት እና አስተሳሰብ ለውጥ አስፈላጊ ክፍል ነው፡፡
1.5 የማስተካከያ ሥራው ተሳትፎ
በወ/ው/ጽ/ቤት እና በፌዴሬሽን ተሳትፎ የተዘረዘሩ የማስተካከያ ሥራዎች በጥገና ዘመቻ ወቅት የሚፈቱ ይሆናሉ፡፡
1.6 የጊዜ ሠሌዳ/ካላንደር
ይህ ዘዴ በጥቅምት እና ኅዳር የሚከናወኑትን ከጥገና ጋር ተያያዥ የሆኑ ተግባራትን ቅደም ተከተል እንደሚከተለው ያብራራል፡-
This document sets out the first stage of the maintenance campaign, how to implement each step, who is responsible, which documents to complete and how the coaching system works.
Key definition
Identify the network problems, by assessing and documenting using the Diagnosis Checklist. The diagnosis of all WP is completed in Tikimnt and helps to define the corrective measures required.
Measures that need to be conducted to solve the problems identified in the diagnosis stage.
Corrective measures can be:
for example - There is a pipe uncovered; the corrective measure is to build a dry wall and backfill
for example - Water point is muddy = organise daily cleaning
The grade is used to reflect the overall diagnosis results, which can be easily seen in the dashboards and reported to WWO. The grading system is explained in more detail below.
A coaching system is an important component of the entire maintenance process and mindset, with specific actions at each step.
A formal engagement by the federation towards the WWO of the list of corrective measures they will address during the maintenance campaign.
This methodology deals with the maintenance related activities to be carried out in Tikimnt and Hidar as set out in the calendar below:
2.1 የፍተሻ ዓየነቶች
ፍተሻ እና የማስተካከያ ሥራ ለሁሉም የሚሠራ ቦኖ ለእያንዳንዱ ፌዴሬሽን መሠራት ይኖርበታል፡፡
የፍተሻ ሥራውም መከናወን ያለበት ከምንጭ እስከ ቦኖ ድረስ፣ የቧንቧ መስመር ተከትሎ ሁሉንም የተቋሙን ክፍሎች ቅኝት በማድረግ መሆን ይኖርበታል፡፡
የተቋሙን መዋቅር ብቻ ፍተሻ አድርጎ በኔትዎርኩ ላይ ከፍተኛ ችግር ሊያስከትሉ የሚችሉ ለምሳሌ ያልተቀበረ ቧንቧ፣ የወንዝና መንገድ መሻገሪያዎችን ቸል ማለት ፍተሻውን ሙሉ አያደርገውም፡፡
2.2 ኃላፊነት
የኔትዎርክ ፍተሻ መደረግ ያለበት የቧንቧ መስመሩን ተከትሎ እስከ ቦኖ ድረስ ሲሆን ሁሉንም የተቋሙን ክፍሎች ቅኝት በማድረግ የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ ከውሃ ተጠቃሚ ማህበራት ጋር በጋራ በመሆን ይኖርበታል፡፡
ይህንን ተግባር በዋናነት ማከናውን የለበት የውሃ ተጠሪ ነው፡፡
የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ ሥልጠና/ድጋፍ የመስጠት (የቴክኒክ እና የአስተሳሰብ ለውጥ የማምጣት ክህሎት የማስተላለፍ) እና ውሃ ተጠሪውን የመቃኘት/የመቆጣጠር ኃላፊነቱን ይወስዳል፡፡
የውማ ፍተሻ በሚደረግበት ወቅት በጋራ ይከታተላሉ፡፡
2.3 መረጃ ማደራጀት
የውሃ ተጠሪው n°WS3-F11-V1.0 “የፍተሻ ቼክሊስቱን ይሞላል፡፡(የፍተሻ መዝገቡ መኖሩን እና መደራጀቱን እንዲሁም ለአንድ ተቋም አንድ ገጽ መኖሩን አረጋግጥ)፡፡
የውሃ ተጠሪው ቼክ-ሊስቱን እያንዳንዱን መስመር ድምጹን ከፍ አድርጎ በሚያነብበት ወቅት የውማ አባላት በመስማት ችግሩን በአካል ይመለከታሉ፡፡
ለምሳሌ፡-
የተፋሰስ ሥራ ማስፈለግ አለማስፈለጉን መለየት የሚችሉት ከሚንጩ በላይ በኩል ሄደው በመመልከት ይሆናል፡፤
በምንጭ ሳጥን ውስተጥ ደለል እና ሥራሥር መኖር አለመኖሩን ማረጋገጥ የሚቻለው የምንጩን ሳጥን ከፍቶ በማየት ይሆናል
የትርፍ ውሃ ማስወገጃ መደፍን አለመደፈኑን ማረጋገጥ የሚቻለው ወደ ትርፍ ውሃ መውጫ ጫፉ ጋር በመሄድ ይሆናል
ውሃ ተጠሪው ቲክ √ ከማድረጉ በፊት ቡድኑ ስለሚፈተሸው ክፍል በሙሉ መስማማት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ትንሽ ችግር ከተገኘበት X ይደረጋል፡፡
ፍተሻው ሲደረግ ካልተስማሙ ወይም ችግር ካለበት (X)፣
ምሳሌ፡-
ችግሩን ለመቅረፍ አንድ ብቸኛ የማተካከያ ሥራ ልንተገብር ይገባናል፡፡
ወንዝ/ሸጥ ሲሻገር ያልተሸፈነ ቧንቧ ካለ = ቧንቧ የተጋለጠበት ቦታ ላይ ካብ መገንባት እና አፈር ማልበስ(ቴክኒካል ሥራ)
ወይም ሁለቱንም ቴክኒካል የማስተካከያ ሥራ እና መደበኛ እንክብካቤ ማሻሻያ ሥራ በጥምረት ልያስፈልግ ይችላል፡፡
The diagnosis and identification of corrective measures must be carried out for all ʻFunctional Water Pointʼ of each federation.
The diagnosis of the network must be conducted from the spring down to each WP, following and checking the pipeline and structure.
A diagnosis of the structure alone (without full check of pipeline) is not a real diagnosis and will not identify the most important risks to the network, which are unburied pies, crossings of gullies and roads.
Network Diagnosis must be conducted from the spring down to each WP following and checking the pipeline and the structure along the way and must be accompanied by members of the WUA.
The Water Agent is responsible for carrying out this work.
The WWO expert is responsible for coaching (transfer technical skills and mindset) and supervising the Water Agent.
The members of the WUA are present for the network diagnosis.
The Water Agent will fill the Format n°WS3-F11-V1.0 “Diagnosis checklist” (make sure it is present and organized in the WUA Book, 1 page per structure).
The Water Agent will read aloud each line of the checklist so that all WUA members can participate and will accompany the WUA to visit where the problem might be found.
Example:
Catchment area protection: will be seen only if the team goes to see above the spring
No silt or roots in spring box: will be seen only if the spring box is open
Overflow is not clogged and in good state: will be seen only if the team goes to see downstream to the evacuation location
The team must agree that everything regarding this checklist item is perfect for the water agent to tick √.If there is the slightest issue (not perfect) the water agent has to tick X.
If there is a problem (X), the Water Agent asks the team:
Example:
To solve a problem, there might be the need to implement only one type of corrective measure:
Or it might need the combination of corrective technical measures and correction of the periodic care
3.1 ኃላፊነት
በፍተሸ ወቅት አንዴ የማስተካከያ ሥራው ከተለየ በኋላ የውሃ ተጠሪው በአግባቡ መዝግቦ ልይዛቸው ይገባል፡፡
ይህም መከናወን ያለበት፣ የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ ባለበት በመስክ አልያም እሱ በሌለበት እንደሆን በፌዴሬሽን ቢሮ ሊሆን ይገባል፡፡
3.2 መረጃ አያያዝ
The Format n° WS3-F12 ማስተካከያ ሥራ መከታተያ ፎርማትን የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያው መሙላት ይኖርበታል
Once the corrective measures have been identified at the diagnosis stage, the Water Agent must document them formally.
This is done either in the field (for the network where the WWO expert is accompanying), or in the WUAF office for the other networks.
The Format n° WS3-F12 Corrective Measure Follow-up filled in by the WWO Expert .
</WRAP>
❶ የተቋም ዓይነት( ለምሳሌ፡ ማጠራቀሚያ) እናተቋሙ በማኅብረተሰቡ የሚጠራበትን ስም ጻፍ
❷ በቼክ-ሊሰቱ ላይ የተለዩ ችግሮችን ጻፍ( እያንዳንዱን ቼክሊስት በ X ጻፍ )
❸ ከመደበኛ እንክብካቤ ጋር የተያያዘውን ችግር እና የመደበኛ እንክብካቤ ለውጥ የሚፈልገውን ቲክ አድርግ(ከታች ያለውን የመደበኛ እንክብካቤ ክፍል ተመልከት)
❹ የማስተካከያ ሥራ የሚያስፈልገውን ዘርዝር፡፡ የቴክኒክ እነ መደበኛ እንክብካቤ ሥራ የሚያስፈልግ ከሆነ፣ ሁለት መሰመሮችን ተጠቀም፤ አነዱን መስመር ለአንዱ ማስተካከያ ሥራ
❺ የተኛው ሥራ በማን ይመራል የሚለውን ተገቢውን ሳጥን ለተገቢው ሰው ቲክ አድርግ
❻ በፍተሻ ቼክሊስቱ ላይ በግልጽ እንደተብራራው መደበኛ እንክብካቤ የጊዜ ሠሌዳ ያለ እንደሆን አዎን ብለህ ጻፍ
መሬት ላይ ከተተገበረ(አዎን)
ለምሳሌ፡-
በዚህ መሰረት መደበኛ እንክብካቤ ለማድረግ መታሰቡን ነገር ግን አለመተግበሩን
ጥንቃቄ፡ በዚህ ደረጃ የውሃ ተጠሪው በኋላ ላይ ሊቀረፉ የሚችሉ ችግሮችን ለይቶ የማስተካከያ ሥራዎችን መንደፍ ይኖርበታል፡፡
ለመደበኛ እንክብካቤም ተመሳሳይ ሎጂክ ልንከተል ይገባል፡፡ ሥራውን የማደራጀትና ተግባራዊ የማድረጉ ጉዳይ ምንም እንኳን ከኋላ ቢሆንም የውሃ ተጠሪው በችኮላ ወዲያውኑ በችኮላ ለመሥራት መነሳት የለበትም፡፡
❶ Write the type (ex: reservoir) and the community name of the structure
❷ Write each problem identified in the checklist (each list item with X)
❸ Tick if the problem is linked with periodic care and needs periodic care changes (see section periodic care below)
❹ Describe in detail the corrective measure required. If there is a need for technical measure and periodic care measure, use two lines with one corrective measure per line.
❺ Define who is responsible leading each action by ticking the relevant box for each actor.
❻ Write Yes (Y) if there is a periodic care table clearly defined in the Diagnosis Checklist
Write Yes (Y) if it is properly applied on the ground
Example :
Then periodic care is formalized BUT not effective:
Careful: at this stage, we want the Water Agent to identify problems and propose (jointly with experts) corrective measures to be implemented later.
The same logic applies to periodic care: its organisation and formalisation will be carried out later and must not be done hastily by the Water Agent on the spot.
</WRAP>
የደረጃ አሰጠጥ አጠቃላይ የፍተሻ ውጤት ማሳያ ሆኖ በቀላሉ በደሽቦርድ የሚገለጽ እና ለወ/ው/ጽ/ቤት በሪፖርት የሚገለጽ ነው፡፡
The grade is used to reflect the overall diagnosis results, which can be easily seen in the dashboards and reported to WWO.
ማስጠንቀቂያ፡ ደረጃ በቀጥታ ምን እይነት ሥራ መሠራት እንዳለበት ለማወቅ አይጠቅምም፡፡ የማስተካከያ ሥራ መከታተያ ፎርማት ምን አይነት ሥራ መሠራት እንዳለበት የሚያብራራ ማጣቀሻ ሰነድ ነው፡፡
Careful: grade only does not help to know which exact actions need to be carried out. The Corrective Measure Follow-up format is the document of reference to define what has to be done.
ምሳሌ፡-
ቢያንስ አንድ የማስተካከያ ሥራ ኖሮት በውተ እና በፌዴሬሽን ሊሠራ የማየችል ነው፡፡ ስለዚህ ፌዴሬሽኑ ልምድ ባለው ኮንትራክተር ሥራውን ሊያሰራ ግድ ነው፡፡ነገር ግን በየዕለቱ የጽዳት ሥራውን በራሱ ሊሠራ ይገባል፡፡(በደበኛ የቦኖ እንክብካቤ ሥራ ሊሠራ ይገባል፡፡)
Example :
In this case, the grade of the WP is C as there is at least 1 corrective measure that cannot be managed by the WA and the WUAF, and therefore the federation must contract an experienced mason.
However it is mandatory for the WUAF to correct the daily cleaning (implementing the WP periodic care).
ለእያንዳንዱ ተቋም ደረጃው በማስተካከያ ሥራው መከታተያ ፎርማቱ ላይ ሊሞላ ይገባል፡፡
የተቋሙ አንዱ ወቅር ብቻ ደረጃ፣ የደረጃ አሰጣጡ ከዚህ በታች በተቀመጠው ደንብ መሠረት የተቋሙ አንዱ ውቅር ብቻ ደረጃ ከውቅሩ በላይ ያለውን ቧንቧ ጭምር ያካተተ ደረጃ ነው፡፡(ከቦኖ ራስጌ በኩል ያለው የኔት ዎርኩ እዱ ውቅር እና በካከላቸው ያለ ቧንቧ ጭምር ያካትታል)
የሚሠራ ተቋም ሆኖ ምንም አይነት የማስተካከያ ሥራ የሌለው ወይም ሁሉም የማስተካከያ ሥራ የተሠራለት ተቋም ነው፡፡
አንድ ቦኖ ውሃው በሚመጣበት አቅጣጫ(ራስጌ በኩል) በላይ በኩል ያሉት ችግሮች በሙሉ የቦኖው የራሱ ችግር ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ ደረጃውም ከዚሁ ከራስጌ በኩል ካሉት የኔትዎርኩ ክፍል የከፋው ችግር ያለበት ደረጃ ይሰጠዋል፡፡
ይህ ሪፖርት የተደረገው የቦኖ ደረጃ የቦነውን የራሱንና ከቦኖው በላይ በኩል ያለውን የኔትዎርክ አጠቃላይ ሁኔታ ያመላክታል፡፡
For each structure the grade is filled out on the Corrective Measure Follow-up format:
The structure only grade: the grade is defined by the rules set out below for the structure itself as well as for the upstream pipeline (the pipe between the upstream structure and the WP).
A water point inherits all the problems identified upstream and therefore, the overall WP grade is the worse of either the WP only grade or the worst upstream grade.
This overall WP grade is the one reported, as it provides information on the real condition of both the WP and the network upstream.
ፍተሻ፣የማስተካከያ ሥራ ልየታ እና ፈር ማስያዝን በተሳካ መልኩ ለመተግበር የሚከተለውን የሥልጠና/ድጋፍ ሥርዓት ፣ከተል ይኖርብናል
To enable the successful implementation of the diagnosis, identification and formalisation of corrective measures, the following coaching system is in place:
ደረጃ 1፡ ክልል ግብረ-ኃይል እና የአርአያ ማስተባበሪያ
ተሳታፊዎች፡
የአንድ ቦኖ ፍተሻ እና የማስተካከያ ሥራ ልየታውን(ከምንጭ አስከ ቦኖ) በአንድ ፌዴሬሽን ለየዞኑ ገለጻ ማድረግ
ደረጃ 2፡ የዞኑ ባለሞያ እና የዞኑ አርአያ ባለሞያ
ተሳታፊዎች፡
የአንድ ቦኖ ፍተሻ እና የማስተካከያ ሥራ ልየታውን(ከምንጭ አስከ ቦኖ) በአንድ ፌዴሬሽን ለየወረዳው ገለጻ ማድረግ
ደረጃ 3፡ የወረዳ አርአያ ድጋፍ → ለወረዳ ባለሞያ
ተሳታፊዎች፡
በየትኛውም ወረዳ ባለሞያ የሚደረገው የመጀመሪያው ፍተሻ እና የማስተካከያ ሥራ ልየታ(ከምንጭ እሰከ ቦኖ) መደረግ ያለበት በወረዳ አርአያ ባለሞያ ድጋፍ መሆን አለበት
ደረጃ 4፡ የወረዳ ባለሞያ ድጋፍ
5.1.መረጃ ማደራጀት
በዚህ ደረጃ የሚከተሉ መረጃዎች ሊደራጁ ይገባል
- በመስክ የሚሞላ የፍተሸ የፍተሻ ቼክሊስት፡ Format n°WS3-F11-V1.0 Diagnosis checklist format - በወረዳ ባለሞያ የሚሞላ የማስተካከያ ሥራ መከታተያ ፎርማት፡ Format n° WS3-F12 Corrective Measure Follow-up - በሠንጠረዡ መጀመሪያው የቁም ረድፍ የሚሞላ Format n° WS3-F15: Maintenance Plan፡፡ የተቋሙን ስም እና ዓይነት እንዲሁም የሚተገበር የማስተካከያ ጥገና መሙላት፡፡ - የወረዳ ወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያው የፍተሸ መከታተያውን Format n° WS3-F21 Monitoring – Diagnosis ማጠናቀርና ለወረዳ ማኔጅመንት ቡድን እና ለዞኑ ፎካል ክትትል ለማድረግ እንዲመች መላክ ያስፈልጋል
Step 1: RTF & ARIA Coordination
Participants:
Conduct a Diagnosis and Corrective Measure Identification for one WP (Spring to WP) in one federation per Zone.
Step 2: Zone expert and ARIA Zone expert
Participants:
Conduct a Diagnosis and Corrective Measure Identification for one WP (Spring to WP) in one federation per Woreda.
Step 3: ARIA Woreda Supporter → WWO expert
Participants: → Participants :
The first Diagnosis and Corrective Measure Identification (Spring to WP) of every WWO Expert is supported by ARIA Woreda Supporter.
Step 4: WWO expert support
As a summary the following documents must be produced at this stage:
- Diagnosis checklist filled in the field by the Water Agent: Format n°WS3-F11-V1.0 Diagnosis checklist format - The Format n° WS3-F12 Corrective Measure Follow-up filled in by the WWO Expert - The first column of the Format n° WS3-F15: Maintenance Plan - Fill the structure name and type as well as the number of corrective maintenance actions required. - The WWO expert compiles the diagnosis monitoring format Format n° WS3-F21 Monitoring – Diagnosis and shares it with the WMT and the Zone focals for monitoring.
6.1. ከፌዴሬሽን ጋር በጋራ መሥራት
የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ የወረዳ ማኔጅመንት ኮሚቴ በተገኘበት Doc n° WS3-M11a “የፍተሻ እና የማስተካከያ ሥራ በተመለከተ ማብራሪያ ለፌዴሬሽን ይሰጣል፡፡
The WWO expert presents the Doc n° WS3-M11a “Presentation of diagnosis and corrective measures to Federations” to the federation committee, in the presence of the WMT, and gives them a copy.
6.2 ሕጋዊነት ማልበስ
ሁሉም ኔትዎርክ አንዴ ከተፈተሸ እና በማስተካከያ ሥራ ፎርማቱ ላይ ተመዝግቦ ሕጋዊ ከሆነ በኋላ የማረጋገጥ እና የማሳወቅ ሥራው ለውማፌ እና ለወማኮ ከተደረገ በኋላ በመፈራረም ወደ ሥራ ይገባል፡፡
ተሳታፊዎችና ኃለፊነቱን የሚወስድ አካል
የስብሰባው ዋና አጀንዳዎች
- የእያንዳንዱን ኔትወርክ የማስተካከያ ሥራ ውሃ ተጠሪው በወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ ድጋፍ ገለጻ ያደርጋል - ፌዴሬሽንና የውማ ተወካይ የማስተካከያ ሥራውን ተገቢነት በማረጋገጥ በሂደቱ ተሳትፎ በማድረግ ችግሩን ይፈታሉ፤ የፌዴሬሽኑ ሰብሳቢ ማስተካከያ ሥራውን ለመፍታት በፊርማ ያረጋግጣል( Format n° WS3-F12 Corrective Measure Follow-up.) - የወማኮ ተወካይ ሁሉንም ዓይነት የማስተካከያ ሥራ ያረጋግጣል፤ ምንም ዓይነት የማስተካከያ ሥራ በሠንጠረዡ የC ቁም መስመር ያለመካተቱን በማረጋገጠ መፈረም
ሁሉም ባለድርሻ አካላት የማስተካከያን ሥራውን ለመሥራት መስማማታቸውን በፊረማ ሲያረጋግጡ
- የኔትወርኩን ወጣይነት ማረጋገጥ የሚችሉ ጉዳዮች ታሳቢ መደረግ ይኖርባቸዋል
- የውማ፣ውማፌ እና የወ/ው/ጽ/ቤት ሁሉም የB ማስተካከያ ሥራዎችን በራሳቸው አቅም ሊሠሩ ይገባል፡፡(ይህ ካልሆነ ግን ፌዴሬሽኑ በጥገናው ሊወድቅ ይችላል)
- የውማ፣ውማፌ እና የወ/ው/ጽ/ቤት ቢያንስ አንድ የC ማስተካከያ ሥራ መርጠው በራሳቸው አቅም ሊሠሩ ይገባል፡፡(ይህንን ካደረጉ ፌዴሬሽኑ በዳሽቦርዱ አንድ ነጥብ ያገኛል)
Once all networks have been diagnosed and all corrective measures identified and formalised in the corrective measure follow-up format, a presentation and validation meeting is organised to present them to the WUAF and the WMT, who must then endorse and sign them.
Participants and responsibilities:
Content of the meeting:
- Network per network, the Water Agent presents all the corrective measures (supported by the WWO expert). - The federation and WUA representative must approve that these corrective measures are appropriate and engage themselves to address them → The WUAF president signs the Format n° WS3-F12 Corrective Measure Follow-up.
3. The WMT representative must validate the overall corrective measures, verify that there is no corrective measure abusively entered under the C column and sign the document.
By signing this document all parties recognise that :
ለ. ማላመድ/ማብቃት
የማላመድ ሥራው በቢሮ ደረጃ ብቻ ካበቃ ሙሉ ክህሎትና እውቀት ሊያስጨብጭ አይችልም
ደረጃ 1፡ የክልሉ ግብረ-ኃል እና የአርአያ ማስተባበሪያ
ተሳታፊዎች፡
የልምምድ ጊዜ ማመቻቸት፡ በቢሮ ደረጃ የቲዮሪ እና በመስክ ደረጃ የልምምድ ጊዜ ማመቻቸት
ደረጃ 2፡ የዞን እና የአርአያ ዞን ባለሞያ
ተሳታፊዎች
ስለሥራው ትውውወቅ በወረዳ ቢሮ ደረጃ ማድረግ እና የመጀመሪያውን የመስክ ልምምድ በዞኑ ባለሞያ ድጋፍ ማድረግ
ደረጃ 3፡ የወረዳ አርአያ ደጋፊ → ወ/ው/ጽ/ቤት
የመጀመሪያው ወ/ው/ጽ/ቤት የመስክ ልምምድ በወረዳው አርአያ ባለሞያ ድጋፍ ይደረጋል
ደረጃ 4፡ ቀሪ ልምምዶች
የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ እና የወማኮ በሁሉም ፌዴሬሽን በመገኘት ልምምዱን በቀሪ ፌዴሬሽኖች በማካሄድ ይጨርሱታል፡፡
ሐ. መረጃ ማደራጀት
በ Format n° WS3-F15: Maintenance Plan በተሰኘው ሠንጠረዡ የመጀመሪያ ቁም መስመር ሁሉንም በፌዴሬሽን የሚከናወኑ ተግባራትን ማግኘት ይቻላል፡፡ የተቋሙን ስምና ዓይነት እንዲሁም የማስተካከያ ሥራዎችን መጠን በዚሁ መሙላት ያስፈልገል፡፡
የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ ፊርማ ተደረገበትን ሰነድ ፎቶ በማንሳት Format n° WS3-F12 Corrective Measure Follow-up በተሰኘው ፎርማት በማደራጀት ለዞኑም ባለሞያ ጭምር መላክ ያስፈልጋል
As this is an office based activity, the coaching process can be lighter:
Step 1: RTF & ARIA Coordination
Participants:
Organise a coaching session in office with only theoretical training and practical case study (role play)
Step 2: Zone expert and ARIA Zone expert
Participants:
Orientation session held at Woreda Office, and a first practical session where the Zone Expert supports the organisation of the meeting on site.
Step 3: ARIA Woreda Supporter → WWO expert
The first meeting of every WWO Expert is supported by ARIA Woreda Supporter.
Step 4: Remaining meetings
WWO Expert and WMT members conduct the meetings in all remaining federations.
The first column of the Format n° WS3-F15: Maintenance Plan can be used to help present the overall work required to the federation. Fill the structure name and type as well as the number of corrective maintenance actions required.
The WWO expert takes a picture of the signed Format n° WS3-F12 Corrective Measure Follow-up, files it and sends a copy to the Zone expert.