Spring Pre-Excavation
Procedures:
- Before digging, federation should sign land use permit agreement with owner(s) of the land where the spring is located. This permit protects federation in the future and secures compensation for the owner(s).
- Latrine coverage in the Kebele should be checked, no constructions will begin without à 90% coverage.
- Community mobilization is key for an efficient digging.
- During rainy season soil can easily slide when vegetation is removed, so they should consult Scheme admin and woreda construction experts
የምንጭ የመጀመሪያ ዙር ቁፋሮሂደቶች**
- ቁፋሮ ከመጀመሩ በፊት ፌዴሬሽኑ ምንጩ ከሚገኝበት የመሬት ባለቤት ጋር የመሬት ፈቃድ ስምምነት መፈራረም ይኖርባቸዋል።ስምምነቱ የመሬቱ ባለቤት ተገቢውን ካሳ እንዲያገኝ የሚያደርግ እና ለወደፊት ፌዴሬሽኑ ዋስትና እንዲኖረው የሚያደርግ ይሆናል።
- የቀበሌው ወይም የምንጩ ተጠቃሚዎች የሽንት ቤት ሽፋን መታወቅ ይኖርበታል፡የሽንት ቤት ሽፋን 90% ካልደረሰ ግንባታ የማይጀመር መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል።
- ዉጤታማ ቁፋሮ ለማድረግ የህብረተሰቡ ንቅናቄ ወሳኝ ነው
- በቁፋሮ ወቅት ሊገጥም የሚችል ችግር ይኖራል ብለው የሚያስቡከሆነ የወረዳ ተቋማት አስተዳደር እና የግንባታ ቁጥጥር ባለሞያወችን ማማከር ያስፈልጋል።
First step is to locate precisely the point where the water is coming out of the ground.
መጀመሪያ ምንጩ የሚፈልቅበትን ትክክለኛ ቦታ መለየት
Then the area surrounding the spring must be cleared to create a suitable working area (at least 5m all around the point located above). Trees, bushes, crops, grass must be removed.
የምንጩን ዙሪያ ማፅዳትና ለስራ ምቹ ማድረግ ከዚያም በምንጩ ቢያንስ 5ሜ ወሰን የሚገኘውን ማንኛውንም ዛፍ፡ቁጥቋጦ፡ሳር የመሳሰሉትን መመንጠር እና ማስወገድ
Site clearing
የምንጭ ዙሪያ ምንጣሮ እና ፅዳት
Dig a 50cm wide evacuation canal for the water, depth should be defined according to flow. This allows the sediments to evacuate outside of the digging zone. There should be no stagnant water during the digging.
ሴ.ሜ ስፋት ያለው ማፋሰሻ ቦይ መቆፈር። ይህ ቦይ በቁፋሮ ወቅት አፈሩን ለማስወገድ እና ዉሃ የሚቆፈረው ቦታ ላይ እንዳይተኛ እና ለስራ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል
Start digging a trench from the located point towards the slope. Remove all the rocks and regularly unclog the evacuation canal.
ቁፋሮውን ከምንጩ አይን ጀምሮ ወደ ላይ መቆፈር።የማፋሰሻ ቦዩ እንዳይደፈን በየጊዜው ማፅዳት
The spring excavation shall be done carefully not to disturb the spring eyes. The excavation continues from bottom to upward following the water until spring eyes outlet are well defined.
የምንጭ አይን ቁፋሮ የምንጭ አይኑ እንዳይጠፋና አቅጣጫዉን እንዳይቀይር በጥንቃቄ ከታች ወደ ላይ የምንጩን አይን በመከተል ትክክለኛው የምንጭ አይን እስኪገኝ ድረስ መቆፈር ይኖርበታል
Keep on digging following incoming water locations. It might come out of several places, widen the trench accordingly.
የምንጩን ፍሰት በመከተል ቁፋሮዉን አጠናክሮ መቀጠል።የምንጩ ፍሰት ከተለያየ አቅጣጫ ከሆነ ቁፋሮዉን ፍሰቱን ተከትሎ ሰፋ አድርጎ መቆፈር
When there is side flow, to minimize the excavation, side excavation recommended. Excavate from bottom to top
የምንጭ ፍሰት በጎን በኩል በሚኖርበት ጊዜ ምስሉ ላይ እንደሚታየው ቁፋሮዉን በጎን በኩል ፍሰቱ ወደ አለበት ማስቀጠል
Example of finished side digging (T trench)
በጎን በኩል ያለን ቁፋሮ የሚያሳይ ምስል
The preliminary digging is finished when you reach hard strata and approach the eyes of the spring (points where you can see the water coming above the ground).
At this point The Woreda construction experts have to be consulted to support the community by giving orientation and guidance on how the community finish the excavation and the eyes clearance.
የምንጭ የመጀመሪያ ዙር ቁፋሮ የሚጠናቀቀዉ የላይኛው አፈር ከተነሳ በኃላ የምናገኘው የአፈር አይነት ጠንከራና አለታማ ሲሆንና የምንጩ አይን በትክክል አለታማ ከሆነው አፈር የሚወጣ መሆኑ ሲታወቅ ነው።
የመጀመሪያ ዙር ቁፋሮ ከመጠናቀቁ በፊት የወረዳ ተቋማት አስተዳደር እና የወረዳ ግንባታ ባለሞያዎችን ማማከር እና እገዛቸውን መጠየቅ ያስፈልጋል