SouthEthiopiaFlag
PROCEED
CentralEthiopiaFlag

southlogo.jpeg

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ኢትዮጵያ ነጋሪት ጋዜጣ

DEBUB ETHIOPIA NEGARIT GAZETA OF THE SOUTH ETHIOPIA REGIONAL STATE

ደንብ ቁጥር ፻፩ /፳፻፲፰ ዓ.ም

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበር፣የማህበራት ፌዴሬሽንና የብዝሀ ቀበሌ ማቋቋሚያ ደንብ

Regulation No. 101/2026

Rural Potable Water and Sanitation Associations, Federation and Multi-Kebele Establishment Regulation

መግቢያ

የክልሉን የዉሀ ሀብት አጠቃቀም ከሀገሪቱ የውሀ ሀብት አስተዳደር ፖሊሲ ጋር የሚጣጣም የመጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት አሠጣጥ ስርዓት መዘርጋት በማስፈለጉ፣

Preamble

Whereas; it has become necessary to establish a potable water and sanitation service provision system that aligns the utilization of the region’s water resources with the country’s water resources management policy;

በክልሉ ያለውን የዉሀ ሀብት በፍትሐዊነትና አግባብነት ባለው መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል አስፈላጊ በመሆኑ፤

Whereas; it is necessary to utilize water resources of the region in a fair and proper manner;

በየገጠሩ በመንግሥት፣መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና በኀብረተሰቡ የተገነቡ የውሀ ተቋማት ወጥነት ባለው የአሠራር ሥርዓት ተቃኝተው የሚፈለገውን ጥቅም እንዲሰጡ ማስቻል ተገቢ በመሆኑ፤

Whereas; it is appropriate to enable water schemes that have been built by the government, nongovernmental organizations, and community participation across rural areas to be applied for the desired objective through a harmonized working system;

በገጠር የሚታየውን የተበታተነ የመጠጥ ውሀ ተቋማት አሠራር በማስቀረት የገጠር መጠጥ ውሀ ተጠቃሚዎች የውሀ ሀብታቸውን በአግባቡ የሚጠቀሙበትንና ሕብረተሰቡ በባለቤትነት እንዲያስተዳድራቸው አገልግሎት ሰጪ የውሀ ተቋማት አደረጃጀት እና አሠራርን መወሰን በማስፈለጉ፤

Whereas; it is necessary to determine the organization and working system of potable water schemes so as to avert fragmented working system and thereby the users of rural potable water use their water resource properly and that they administer it in a sense of ownership;

የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበር፣ የማህበራት ፌዴሬሽንና የብዝሀ ቀበሌ የኦኘሬሽንና ጥገና ወጪያቸውን ሸፍነው የሚሠሩበትን ምቹ ሁኔታ መፍጠር ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፣

Whereas, it has become appropriate to create conducive environment that enables to cover operational and maintenance costs of rural potable water and sanitation association, federation and multi-kebele;

በሁሉም የገጠር አካባቢዎች የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበር፣ የማህበራት ፌዴሬሽንና የብዝሀ ቀበሌ የሚቋቋሙበት፣ የሚተዳደሩበትንና የውሀ ሀብት ተጠቃሚ የሚሆኑበትን የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት በማስፈለጉ፣

Whereas; it is necessary to issue a legal framework thereby rural potable water and sanitation association, federation and multi-kebele to be established, administered and to be benefited from water resources;

የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት አስፈጻሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር እንደገና ለመወሳን በወጣው አዋጅ ቁጥር ፰፬//፳፻፲፯ አንቀፅ ፶ ንዑስ አንቀፅ ፩ መሠረት ይህንን ደንብ አዉጥቷል።

Now therefore; in the accordance with Article 45 sub-article 1 of Proclamation No. 84/2024 issued to re-determine the power and duties of the South Ethiopian Regional State Executive Organs, the Executive Council has hereby proclaimed as follows.

ክፍል አንድ ፥ ጠቅላላ

Part One : General

፩. አጭር ርዕስ

ይህ ደንብ “የገጠር መጠጥ ዉሀና ሳኒቴሽን ማህበር፣የማህበራት ፌዴሬሽንና የብዝሀ ቀበሌ ድርጅቶች ማቋቋሚያ ደንብ ቁጥር ፻፩/፳፻፲፰” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል።

1. Short Title This regulation may be cited as “Rural Potable Water and Sanitation Association, Federation and Multi-kebele Regulation No. 101/2026”

፪. ትርጓሜ የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ ደንብ ውስጥ፡- ፩. “ክልል” ማለት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ነው።

2. Definition In this Regulation, unless the context otherwise requires;

1. “Region” means the South Ethiopia Region;

፪. “ቢሮ” ማለት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የውሀና ኢነርጂ ቢሮ ነዉ

2. “Bureau” means Water and Energy Bureau of the South Ethiopia Regional State

፫. “መ/ቤት” ማለት በየደረጃዉ የሚገኙ ለቢሮ ተጠሪ የሆኑ ወይም በሥሩ ያሉ መዋቅሮቹ የዞን ዉሀና ኢነርጂ መምሪያ እና የወረዳ ዉሀና ኢነርጂ ጽ/ቤትን ይጨምራል።

3. “Office” means those structures at various levels which are accountable to the Bureau including the Zone Water and Energy Department and Woreda Water and Energy Office.

፬. “የበላይ ጠባቂ” ማለት የብዝሃ ቀበሌን በበላይነት የሚጠብቅ፣ የሚመራ እና ከቦርድ አባላት ጋር በጋራ የሚሰራ አካል ነው።

4. “Oversight body” means a body that incorporates a government representative that supervises and leads multi-kebele and works with board members.

፭. “ጠቅላላ ጉባዔ” ማለት የአንድ ማህበር ወይም የማህበራት ፌዴሬሽን ከፍተኛ ውሣኔ ሰጪ አካል ነው።

5. “General Assembly” means the highest decision making body of an association, federation or a multi-kebele.

፮ “ቦርድ”ማለት የገጠር ንጹህ መጠጥ ውሃ አገልግሎቱን በበላይነት የሚያስተዳድር ከተለያዩ አካላት የተውጣጣና የተሰየመ ሆኖ ተጠሪነቱ ለቢሮ ነው።

6. “Board” means an entity composed of members selected and assigned from different bodies for the oversight of rural potable water services and it is accountable to the Bureau.

፯. “የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች” ከዚህ በኋላ “አገልግሎት ሰጪ ድርጅት” እየተባለ የሚጠራው በገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ለመስጠት የተቋቋመ ማህበራት፣ የማህበራት ፌዴሬሽን እና የብዝሃ ቀበሌን በጋራ የሚጠሩበት መጠሪያ ነው።

7. “Rural potable water and sanitation service provider organizations” hereinafter “service provider organizations” is a common nomenclature of associations, federations, and multi-kebele organizations established to provide rural potable water and sanitation services.

፰ “የውሀ መገኛ” ማለት የውሀ ተቋማት በተፈጥሮም ሆነ በሰው ሰራሽ መንገድ ውሀ የሚያገኙበት ቦታ ማለት ሲሆን ምንጭ፣ወንዝ፤ከርሰምድር ውሀ እና ሌሎችንም ያጠቃልላል።

8. “Water source” means a place where water is found and includes spring, river, groundwater, and other sources.

፱.”የዉሀ ተቋም” ማለት በየገጠሩ በመጠጥ ውሀ ወይም የሣኒቴሽን አገልግሎት የሚሰጡ የቧንቧ ውሀ፣ የጉድጓድ ውሀ፣ በእጅ ፓምኘ የሚሠራ ቧንቧ፣ የምንጭ ውሀ፣ የመፀዳጃ ቦታዎችና ሌሎች መሠል አገልግሎት ሰጪ ተቋም ነው።

9. “Facility” means a structure where pipe water, underground water, water from hand-pump operation, spring water, toilets and other similar services are being provided.

፲ “የመጠጥ ውሃ ተቋም” ማለት የውሃ ተቋም እየተባለ የሚጠራው የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ለመስጠት የተገነቡ እና የተዘረጉ አጠቃላይ የመጠጥ ውሃ መሰረተ ልማት ግንባታዎችን የሚያጠቃልል ነው።

10. “Potable water scheme” also known as water scheme is an infrastructure constructed to provide potable water service.

፲፩. “ቦኖ” ማለት ተጠቃሚው ለመጠጥ አገልግሎት የሚውል ውሃ የሚቀዳበት ቦታ ነው።

11. “Water point” means a point where users get potable water.

፲፪. “የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ማህበር” ወይም “ማህበር” በገጠር ቀበሌያት የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ተጠቃሚዎች በጋራ በመሆን የሚመሰርቱት የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ማህበር ነው።

12. “Rural water supply and sanitation Association” or “Association” established by potable water and sanitation service users in a rural kebele.

፲፫. “የማህበራት ፌዴሬሽን” ወይም “ፌዴሬሽን” ማለት በአንድ የገጠር ቀበሌ ሁለትና ከዚያ በላይ የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበራትን ያቀፈ አደረጃጀት ያለውና የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው።

13. “Associations’ Federation” or “Federation” means a service provider organization that constitutes two or more water and sanitation associations in a single rural kebele.

፲፬ “ብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ድርጅት” ማለት ወይም “ብዝሀ ቀበሌ” ለሁለት እና ከዚያ በላይ ለሆኑ የገጠር ቀበሌዎች፣ ወረዳዎች ወይም ዞኖች የውሀ መገኛው ከጥልቅ ጉድጓድ፣ ከምንጭ ወይም ከወንዝ የተጠለፈ ሆኖ በአንድ አስተዳደራዊ ወሰን ሳይገደብ አገልግሎት የሚሰጥ የገጠር የንፁህ መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ድርጅት ማለት ነው።

14. “Multi-kebele rural potable water and sanitation organization” or “Multi-Kebele” is a rural potable water and sanitation organization providing services to users of more than one kebele, woreda, or zone through water scheme regardless of administrative boundaries.

፲፭ “ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ” ማለት እንደ አግባብነቱ በገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት የሚሰሩ በጠቅላላ ጉባኤ ወይም በቦርድ የተመረጡ የሥራ አስፈፃሚ አካል ነው።

15. “Executive Committee” means a body, as may be necessary, composed of individuals selected by the General Assembly or by the Board and work for the rural potable water service organization.

፲፮ “ንዑስ ኮሚቴ” ማለት የማህበሩን ወይም የማህበራት ፌዴሬሽኑን ዓላማ ለማስፈፀም እንደአስፈላጊነቱ ከሥራ አስፈፃሚ ስር የሚቋቋም ኮሚቴ ነው።

16. “Sub-committee” means a committee established under the Executive Committee, as may be necessary, to implement the objectives of the association or the federation.

፲፯ “ደረጃ” ማለት የገጠር ውሃና ሳኒቴሽን ብዝሀ ቀበሌ የተጠቃሚዉን ሕዝብ ብዛት እና ወሰን ተሻጋሪነትን መሠረት አድርጎ የሚሰጥ መስፈርት ነው።

17. “Grade” means a level issued by a rural potable water and sanitation multi kebele, based on size and cross border nature of the user population.

፲፰. “ሰው” ማለት ማንኛውም የተፈጥሮ ሰው ወይም በሕግ የሰውነት መብት የተሰጠው አካል ነው

18. “Person” means any natural or legal person.

፫. የጾታ አገላለፅ

በወንድ ጾታ የተገለፀው ድንጋጌ የሴትንም ጾታ ያካትታል።

3. Gender Reference

In this Regulation, any expression in the masculine gender shall include the feminine.

፬. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ ደንብ በክልሉ በተቋቋሙ እና በሚቋቋሙ የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበር፣ ማህበራት ፌዴሬሽን እና ብዝሀ ቀበሌ ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ ይሆናል።

4. Scope of Application

This Regulation shall be applicable on association, federation, and multi-kebele organizations established and to be in the region.

፭ የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅቶች የሚመሩባቸው መርሆች

የመጠጥ ዉሀና ሳኒቴሽን አገሌግልት ድርጅቶች በሚከተለት መርሆች ይመራለ

፩. አባልነት በተጠቃሚነት የተመሠረተና ለሁሉም ክፍት የመሆን፣

፪. የውሀ ሣኒቴሽን አጠቃቀምንና ከብክለት ነፃ የሆነ የውሀ አጠቃቀምን ትምህርትና መረጃ መስጠት

፫. ከሌሎች የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ማህበራትና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ጋር ጤናማ ግንኙነት በመፍጠር ለተሻለ አገልግሎት አሠጣጥ በትብብር መስራት።

፬. አገልግሎት ተቀባይ የገጠር መጠጥና ሳኒቴሽን ማህበራት ለአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነትና ግዴታ የመወጣትና ጤናማ ግኑኝነት የመፍጠር፣ የሚጠበቅባቸውን ኃሊፊነትና ግዳታ የመወጣትና ጤናማ ግኑኝነት የመፍጠር፣

፭. አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች የሚያቀርቧቸውን የውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት በጥራት፣በበቂና ዘላቂነት ባለው መልኩ የማቅረብ፣

፮. ከመጠጥ ውሀ አገልግሎት የሚሰበሰበው ገንዘብ ግልፅነት ያለው ሕጋዊነትን የተከተለና ወጥነት ያለው ማድረግ የሚሏቸው መርሆዎች ይመሩባቸዋል።

5. Guiding Principles

Principles guiding rural potable water and sanitation organizations shall be the following.

1. Membership shall be based on benefits of members and open for all;

2. Providing education and information on the pollution free use of potable water and sanitation;

3. Work in collaboration with other associations and service provider organizations for a better service delivery;

4. Establishing healthy relationships between service recipient rural potable water and sanitation associations and service providing organizations and fulfillment of responsibilities and obligations of the former to the latter;

5. Provision of quality, adequate and sustainable water and sanitation services by the service provider organizations;

6. Application of the principles of transparency, legality, and consistency for the fees collected from potable water services.

፮. የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅቶች የሚከተሉት አደረጃጀቶች ይኖራቸዋል

፩. የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበራት

፪. የቀበሌ ገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበራት ፌዴሬሽን

፫. ብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ድርጅት

6. Organization of Service Providing Organizations

Service providing organizations shall have the following structure.

1. Association

2. Federation and

3. Multi-kebele

ክፍል ሁለት ፥ ስለገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበራት አመሠራረትና ምዝገባ

Part Two : Establishment and Registration of Association

፯. የገጠር መጠጥ ውሀና ሣኒቴሽን ማህበራት በሚከተሉት ይደራጃል።

፩. ጠቅላላ ጉባዔ

፪. ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

፫. እንደ አስፈላጊነቱ ንዑሳን ኮሚቴዎች ወይም ሠራተኞች ይኖሩታል።

7. Association shall have following Structure:

1. General assembly;

2. Executive committee and

3. Sub committees and other staffs as may be necessary.

፰. የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበር አመሰራረት:

፩. የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበር በአንድ ገጠር ቀበሌ ውስጥ የመጠጥ ውሀ አገልግሎት በሚሰጥባቸው ውሀ መገኛ ልክ ማህበር ይመሰረታሉ።

፪. የገጠር መጠጥ ውሀ ተቋሙን የሚጠቀሙ ቋሚ ተጠቃሚዎች በሙሉ የማህበር አባል የመሆን ግዴታ አለባቸው።

፫. በቀበሌ ውስጥ ያሉ ሁሉም የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ተቋማት በማህበር ይታቀፋሉ።

8. Establishment of Association

1. Associations shall be established in a rural kebele based on number of water sources where potable water services are provided.

2. All permanent users of the water scheme are obliged to be members of the association.

3. All water schemes in a kebele shall be incorporated in a single association.

፱ ስለማህበር አባላት መብትና ግዴታ

፩. ሁሉም የውሃ ተጠቃሚዎች የማህበር አባላት ሲሆኑ ፣ ውሃ የማግኘት መሰረታዊ መብት አላቸው

9. Right and Duties of Members of Association

1. All water users are members an association and they have basic right to access water.

፪. የማንኛውም ማህበር አባል የሚከተሉት መብቶች ይኖሩታል።

ሀ) ማህበሩ የሚሰጠውን አገልግሎት የማግኘት፣

ለ) በማህበሩ ጉባኤዎች የመካፈልና ድምፅ መስጠት

ሐ) የመምረጥና የመመረጥ መብት፣ሆኖም ዕድሜዉ ከአስራ ስምንት ዓመት በላይ የሆነ

መ) ስለማህበሩ ማናቸዉንም መረጃ የመጠየቅ እና የማግኘት፣

ሠ) በመጠጥ ዉሀና ሳኒቴሽን መስክ ልዩ ልዩ ትምህርቶችንና ስልጠናዎችን የማግኘት

2. Any member shall have the following rights.

a) Accessing the services provided by the association;

b) Participating and voting in the meetings of the association;

c) Electing or to be elected; however a member who is under the age of eighteen years is not legible to be elected as member of the executive committee.

d) Asking and getting any information regarding the association.

e) Obtaining education and trainings opportunities in the field of potable water and sanitation.

፫. ማንኛዉም የማህበር አባል የሚከተሉት ግዴታዎች ይኖሩበታል

ሀ) መተዳደሪያ ደንቡን፣የማህበሩ ዉሳኔዎችና መመረያዎችን የማክበር፣

ለ) ማህበሩ ለሚወሰነዉ ዉሳኔዎች አባሉ ተገዢ የመሆን ግዴታ አለበት፣

ሐ) ለማህበሩ ጥቅም በሚሠሩ ሥራዎች ላይ የመሳተፍ

መ) የመመዝገቢያና የውሃ አገልግሎት መዋጮ ክፍያዎችን የመክፈል፣

ሠ) የማህበሩን ንብረት የመንከባከብና የመጠበቅ፣

ረ) ማህበሩ ለሚያስተላልፋቸው ጥሪዎች ተገቢ ምላሽ የመስጠት።

3. Any member of the association shall have the following duties.

a) Respect the bylaw, decisions and directives of the association;

b) Comply with the decisions of the association;

c) Participate in activities that benefit the association;

d) Pay registration and water service fees;

e) Protect and care for the assets of the association;

f) Respond appropriately for the calls of the association.

፲. የገጠር መጠጥ ውሀ ሳኒቴሽን ማህበራት ኃላፊነትና ተግባር፡-

፩. በየገጠሩ ያሉትን የመጠጥ ውሀ ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አሠራርን በመዘርጋት የማስተዳደር፣

፪. ሁሉንም ቋሚ የውሃ ተጠቃሚዎች በአባልነት መያዝ፣

፫. በገጠሩ ያሉትንም ሆነ ወደፊት የሚሠሩትን የውሀ ተቋማት የዉሀ አገልግሎት ታሪፍ ዉሳኔዎችን ያስፈጽማሉ፤ከውሀ አገልግሎት ታሪፍ የሚገኘውን ገቢ በመሰብሰብ የተሰበሰበውን ገንዘብ መልሶ ለመጠጥ ውሀ አገልግሎት ማስፋፊያ እና ጥገና ወጪ እንዲውል በሕጋዊ ደረሰኝ ለአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ገቢ የማድረግ፣

፬. የሣንቴሽን ሥራዎችን በአካባቢያቸው የማከናወን /መሥራት/፣

፭. አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ንዑሳን ኮሚቴዎችን ማደራጀት

፮. ቢሮው በመመሪያ የሚዘረዝራቸው ሌሎች ኃላፊነትና ተግባራት ይኖራቸዋል።

10. Powers and Duties of Association

1. Establish a system and administer water schemes in rural areas so that they could provide appropriate services;

2. Take all permanent water users as members;

3. Execute water service tariff decisions for existing and future water schemes in rural areas; collect fees from water service and remit the money to service provider organizations via legal receipts. The money collected shall be used for the expansion and maintenance of potable water services;

4. Conduct sanitation works in their vicinities;

5. Organize sub-committees when needed;

6. Shall have other powers and duties that are detailed by a directive to be issued by the Bureau.

፲፩. የባለቤትነት መብቶችን ስለማስተሊለፍ

በመንግሥትም ሆነ መንግስታዊ ባሌሆኑ ዴርጅቶችና በኀብረተሰቡ የተገነቡ ወደፊት የሚገነቡ የመጠጥ ውሀ አገሌግልት ተቋማት በዚህ ደንብ መሠረት ለተቋቋሙት ማህበራት የባለቤትነት መብት ይተሊለፍሊቸዋሌ። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናሌ።

11. Transfer of Ownership

Ownership right of water schemes constructed or to be established by governmental and nongovernmental organizations and the community shall be transferred to the associations established as per this Regulation. Particulars shall be determined by a directive.

፲፪. ከማህበር አባልነት በጊዜያዊነት ስለማገድና ስለመመለስ

፩ ማንኛውም አባል በሚከተሉት ምክንያቶች ከማህበሩ በጊዜያዊነት ሊታገድ ይችላል፡-

ሀ) ማህበሩ የጣለበትን ኃላፊነቶችና ግዴታዎች ባለማክበር፣

ለ) በማህበሩ ላይ ጥፋት በመፈፀሙ ምክንያት ሥራ አስፈፃሚ ሲወሰን ይሆናል፣

ሐ) በዚህ ዉሳኔ ቅር የተሰኘ አባል ለጠቅላላ ጉባኤ ይግባኝ ማቅረብ ይችላል፣

፪ የጥፋቶች ዝርዝር ፣ የቅጣት አይነቶችና ደረጃዎች በመመሪያ ይወሰናል።በጥፋትም ልክ ይጠየቃል።

፫ ያለምንም ጥፋት በራሱ ፈቃድ አባልነቱን የለቀቀ አባል ተመልሶ አባል ለመሆን ከፈለገ በስራ አስፈፃሚው ሲወሰን እና በጠቅላላ ጉባኤ ዉሳኔ ሲፀድቅ ተመልሶ አባል ሊሆን ይችላል

12. Temporary Suspension and Reinstatement of Membership

1. Any member may be temporarily suspended for the following reasons:

a) Not observing the responsibilities and duties imposed by the association;

b) General Assembly decision for offences against the association.

c) A member who is dissatisfied with this decision may appeal to the General Assembly

2. Details of offences, types, and levels of penalties shall be specified by a directive. The offender shall be liable on a par with the offence.

3. A member who committed no fault and has voluntarily resigned from his membership may, upon the decision of the executive committee, and approval of the General Assembly, can be reinstated as a member of the association, if he wishes to do so.

፲፫. ስለ ማህበራት ጠቅላላ ጉባዔ ሥልጣንና ተግባር

፩. ጠቅላላ ጉባዔ የማህበሩን አባላት በሙሉ ያቀፈ ሆኖ የማህበሩ የበላይ የሥልጣን አካል ነው።

፪. የማህበሩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እየገመገመ ውሣኔዎችን ያስተላልፋል፤የሥራ እቅድና በጀት ያፀድቃል።

፫. የማህበሩን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎችን ይመርጣል፤ይሽራል።

፬. የማህበሩን ሕልውና የሚመለከቱ ሌሎች ጉዳዮችን በመተዳደሪያ ደንቡና በመመሪያው የሚዘረዘሩ ተግባራትና ኃላፊነቶች ይኖረዋል።

፭. እንደ አስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎችንና ጥቅማ ጥቅሞችን ይወስናል።

፮. የማህበሩን ሕሌውና የሚመለከቱ ላልች ጉዲዮችን በመተዲደሪያ ደንቡና በመመሪያው የሚዘረዘሩ ተግባራትና ኃሊፊነቶች ይኖረዋሌ።

፯. በሥራ አስፈፃሚ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በማየት የመጨረሻ ዉሳኔ ይሰጣል።

፰. ጠቅላላ ጉባኤ ቢያንስ ሁለት ጊዜ በዓመት ይሰበሰባል፤ አስቸኳይ ሁኔታ ሲፈጠር ደግሞ፣ ከስራ አስፈጻሚ ኮሚቴውና ከአባላቱ በ¼ኛው ጥያቄ መሰረት ልዩ ጉባኤ ሊጠራ ይችላል።

13. Powers and Functions of the General Assembly of Association 1. The General Assembly shall encompass all members of the association and is the higher organ of the association.

2. Evaluates the overall activities of the association and passes decisions; approves plan and budget of the association.

3. Elects and dismisses members of the executive committee of the association.

4. Elects and dismisses those who represent the executive committee and the association in the General Assembly of the federation.

5. Determines various incentives and benefits, as needed;

6. Regarding other issues in relation to the existence of the association, it shall have powers and responsibilities as specified in the bylaw and the directive.

7. The general assembly of association shall make a final decision after reviewing complaints submitted by the Executive committee

8. The general assembly convenes bi-annually; however, it may have extraordinary meetings by the request of one-fourth of its members.

፲፬. የማህበራት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራረጥ

፩. በጠቅላላ ጉባዔው አብላጫ ድምፅ ይመረጣሉ።

፪. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ቁጥር /ብዛት/ ከአምስት እስከ ዘጠኝ ሆኖ የሴቶች ተሳትፎ ትኩረት ይሰጥበታል። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

፫. የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የስራ ዘመን ከ3 ዓመት መብለጥ የለበትም ሆኖም የስራ ዘመኑን የጨረሰ የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴን ለመተካት በሚደረግ ምርጫ ላይ የነባሩ ኮሚቴ አባል የሆነ በጠቅላላ ጉባኤው አባላት ጥንካሬው ከተረጋገጠ በድጋሚ ለሁለተኛ ጊዜ ሊመረጥ ይችላል።ይህም የመጨረሻ ይሆናል።

፬. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 የተቀመጠው የሥራ ዘመን እንደተጠበቀ ሆኖ ተግባራቸዉንና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ መወጣት ካልቻሉ የሥራ ዘመናቸዉ ሳይጠናቀቅ ከኃላፊነታቸው በጠቅላላ ጉባኤው ሊሰናበቱ ይችላሉ፣ በህግም ተጠያቂ ይሆናሉ። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

፭. የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በማህበረሰቡ የተመረጡ ሆነዉ በፈቃደኛነት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸዉ። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

14. Selection of Executive Committee of Association 1. Members of the executive committee shall be elected by majority vote of the General Assembly;

2. The number of the executive committee members shall be between five and nine and ensures women’s participation. Particulars shall be determined by a directive.

3. The term of service of member of the executive committee shall not exceed 3 years; however, a member may be re-elected, if his performance is confirmed by the General Assembly, for a final time.

4. Notwithstanding the provisions of sub-Article 3 of this Article, members of the executive committee who fail to properly discharge their duties and responsibilities may be dismissed from their positions by the General Assembly before the expiry of their term and they shall be held legally liable. Particulars shall be determined by a directive.

5. The executive committee members are elected by the General Assembly and serve on voluntary basis. Particulars shall be determined by a directive.

፲፭. የማህበራት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስልጣንና ተግባር

የማህበራት ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

፩. የማህበሩን ጽ/ቤት ያደራጃል፣

፪. የራሱ ሰብሳቢ ም/ሰብሳቢ እና ፀሐፊ ይመርጣል፣

፫. የጠቅላላ ጉባዔውን ውሣኔ ይፈፅማል ፤ያስፈጽማል፣

፬. የማህበሩን በጀት ያንቀሳቅሳል፣

፭. አስፈላጊ ሰራተኞችን ይቀጥራል፣ ማህበሩ ሠራተኞችን መቅጠር የማይችል ከሆነ የማህበሩ አባላትን ተራ በተራ ያሠራል፣

፮. ለማህበሩ አስፈላጊ የሆኑ ተጨማሪ ተግባራትን ያከናውናል፣

፯. የማህበሩ ንብረቶች/የዉሀ ተቋማት በጠቅላላ በአግባቡ ይጠብቃል እንዲያዙም ያደርጋል

፰. ማህበሩን በመወከል ይከሳል፣ይከሰሳል፣

፱. ማህበሩን በመወከል ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ውል ይዋዋላል፣

፲. እንደአስፈላጊነቱ ለንዑስ ኮሚቴዎች የሥራ አመራር በመስጠት ሥራቸውን ይከታተላል፣.

፲፩. ሪፖርት ለሚመለከታቸው አካላት ይልካል

፲፪. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች በማህበሩ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በግልና በጋራ ኃላፊነት የመውሰድ ግዴታ ይኖርባቸዋል፤

፲፫. ሌሎች በመመሪያ በመተዳደሪያ ደንብ የሚዘረዘሩ ኃላፊነቶች ይኖሩታል።

15. Powers and Duties of Executive Committee of Association

The executive committee of association shall have the following powers and duties:

1. Organizes office of the association;

2. Shall elect its Chairperson and Deputy Chairperson;

3. Implements the decisions of General Assembly and causes their implementation;

4. Transacts the budget of the association;

5. Hires the necessary workers or if the association is unable to hire workers, it assigns members of the association to work on a rotational basis;

6. Performs other necessary activities for the association;

7. Protects all the association’s assets/water schemes and causes their proper management;

8. Sues and be sued representing the association;

9. Represents the association in contracts with third parties;

10. Guides subcommittees as needed and monitors their activities;

11. Submits report to the concerned organs;

12. The executive committee members shall be jointly and severally liable for any damage they cause to the association;

13. Shall have other responsibilities which are detailed in directive or bylaw.

፲፮. ስለ ማህበር መፍረስ

፩. አንድ ማህበር ከሚከተሉት በአንዱ ምክንያት በየደረጃዉ በሚገኙ መዋቅሮች ሲረጋገጥ ሊፈርስ ይችላል፡-

ሀ) በማህበሩ ውስጥ ምንም አባል ወይም የውሃ ተጠቃሚ ከሌለ፣

ለ) የውሃ ተቋሙ መልሶ አገልግሎት መስጠት የማይችል መሆኑ ሲረጋገጥ፣

ሐ) የገጠር መጠጥ ውሀ ተቋማት ወደ ከተማ ውሀ አገልግሎት ደረጃ ሲያድጉ ወይም ሲካተቱ።

፪. የፈረሰ ማህበር ሀብት እዳዎቹ ሁሉ ከተከፈለ በኋላ ቀሪው ሀብት ወደ አገልግሎት ሰጪው ድርጅት ይተላለፋል።

፫. የወረዳዉ ዉሀ ጽ/ቤት ማህበሩ ከፈረሰበት ቀን ጀምሮ ከማህበር መዝገብ ይሰርዘዋል ፣ማህበሩ ከመዝገብ ከተሠረዘበት ቀን ጀምሮ ህልውናውን ያጣል።

፬. በሕገ-ወጥ ተግባር ተሰማርተው የተገኙ የማህበር ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች ማህበሩ ሳይፈርስ በሌላ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች እንዲተካ ይደረጋል።የሚፈፀምባቸዉ የቅጣት ሁኔታ ዝርዝር በመመሪያ ይወሰናል።

16. Dissolution of Association

1. An association may dissolve for any of the following reasons, where it is confirmed by the structures at various levels:

a) Where the association has no member or if there is no water user;

b) Where it is proved that the water scheme can no longer be in service even after maintenance;

c) Where the rural potable water schemes are upgraded to a level of an urban water service;

2. After settlement of all the debts of a dissolved association, the remaining assets shall be transferred to the service provider organization.

3. The Woreda Water Office shall delete the association from the register of associations on the date of its dissolution. The association ceases to exist from the date of its deletion from the register.

4. Members of the executive committee who engaged in illegal activities shall be replaced by other members of the executive committee before the dissolution of the association. Particulars regarding their punishment shall be determined by a directive.

ክፍል ሶስት ፥ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት አደረጃጀት

Part Three : Establishment and Structure of Service Provider Organization

፲፯. የቀበሌ ገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት አመሰራረት፡-

፩. ሁሉም የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበራት የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቱ አባል የመሆን ግዴታ ይኖርባቸዋል።

፪. በአንድ ቀበሌ ውስጥ ከአንድ በላይ የቀበሌ ገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ሊኖር አይችልም።

17. Establishment of Service Provider Organization

1. All associations shall be obliged to be members of the service provider organization.

2. There shall not be more than one service provider organization in a kebele.

፲፰ የገጠር መጠጥ ዉሀ ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ኃላፊነት ተግባር

፩. በየቀበሌዉ ያሉትን የመጠጥ ዉሀ ተቋማት ተገቢዉን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል አሠራር በመዘርጋት የማስተዳደር

፪. ለገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች ገቢ ሊደረግ የሚገባውን የውሀ አገልግሎት ክፊያ የመሰብሰብ፣

፫. በገጠሩ ያሉትንም ሆነ ወደፊት የሚሠሩትን የውሀ ተቋማት ከውሀ አገልግሎት የሚገኘውን የአገልግሎት ክፍያ በመሰብሰብ የተሰበሰበውን ገንዘብ መልሶ ለመጠጥ ውሀ አገልግሎት ማስፋፊያ እና ጥገና ወጪ እንዲውል ማድረግ፣

፬. የሣንቴሽን ሥራዎችን በቀበሌያቸው የማከናወን ወይም መሥራት፣

፭. ቢሮው በመመሪያ የሚዘረዝራቸው ሌሎች ኃላፊነትና ተግባር ይኖራቸዋል።

18. Powers and Duties of Service Provider Organization

1. Setting up a system that enables the proper functioning of the water schemes in each kebele and managing it;

2. Collecting the water service fees and depositing with the service provider organizations;

3. Collecting service fees from existing and future water schemes in rural areas and reinvesting the collected funds in the expansion and maintenance of potable water services;

4. Conducting sanitation activities in their respective kebeles;

5. Performing other activities as per the directive issued by the Bureau.

፲፱. የገጠር መጠጥ ውሃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት አደረጃጀት

፩. የገጠር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ማህበራት ፌዴሬሽን አደረጃጀት

የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር ፌዴሬሽን በአንድ ቀበሌ ውስጥ ሁለት እና ከዚያ በላይ ማህበራትን በማቀፍ የተደራጀ የገጠር የመጠጥ ውሃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ነው

19. Structure of Service Delivering Organization

1. Organization of federation

Federation is a rural potable water service provider organization organized by incorporating two or more associations within a single kebele.

፪. የገጠር የመጠጥ ውሃ ብዝሀ ቀበሌ አደረጃጀት

የብዝሃ ቀበሌ አደረጃጀት በአንድ አስተዳደራዊ ወሰን ሳይገደብ፣ ከአንድ በላይ ቀበሌ፣ወረዳ ወይም ዞን በማገናኘት ሁሉንም በስሩ ያሉትን ማህበራት አቅፎ አገልግሎት የሚሰጥ የገጠር የንፁህ መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ድርጅት ማለት ነው።

2. Organization of a multi-kebele

A multi-kebele organization is a rural potable water and sanitation organization that provides services to all kebele associations organized under it, by connecting more than one kebele, woreda, or zone without being restricted to a single administrative boundary.

፫. ልዩ አደረጃጀት

የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት መሆን የሚያስቸለውን መስፈርት ማሟላት የማይችሉ ሆነው ከዚህ በታች ያሉትን ያጠቃልላል።

ሀ) ከአንድ ዉሀ መገኛ ሁለት እና ከሁለት በላይ ተጠቃሚ ቀበሌያት ካሉና ተቋሙን ለማስተዳደር ዉስብስብ ሁኔታዎችና የአቅም ማነስ ባሉባቸዉ ተቋም ከእያንዳንዱ ቀበሌያት የተዉጣጡ የዉሀ ስራዎችን የሚመሩ የጋራ አሠራር ይዘረጋሉ።ዝርዝር ሁኔታም በመመሪያ ይወሰናል።

ለ) አነስተኛ የውሃ ተቋማት ያላቸውና በየግላቸው ቀበሌያቱ ራሳቸውን ማስተዳደር የማይችሉ ወይም ራሳቸውን ችለው ፌዴሬሽን መሆን የማይችሉ፣

፩. የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር እንደማንኛውም ማህበር መብትና የግዴታ ኖሩአቸው የአጎራባች ቀበሌ የውሃ አገልግሎት ድርጅት አባል ይሆናል።

፪. ይህ አባልነት በማንኛውም ጊዜ በማህበሩ እና በወረዳዉ ጽ/ቤት ሊሰረዝ ይችላል።

3. Special organization

Those structures that do not fulfil the criteria for service providing organization shall be organized in the following manner.

a) In cases where there are two or more kebeles that use the same water source and where there are complex conditions and lack of capacity to manage the water scheme, individuals from each kebele shall be selected to lead the water works by establishing a joint operation. Particulars shall be determined by a directive.

b) Kebeles that have small water schemes and are unable to govern such schemes individually or that cannot establish a federation on their own.

i. The water users’ association shall be a member of the water service organization of the neighboring kebele, having same rights and duties as any other association.

ii. This membership may be cancelled at any time by the association or by the Bureau.

፳. የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ማህበርና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት አደረጃጀት ለውጥ ስለማድረግ

፩. የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ማህበራትና የማህበራት ፌዴሬሽን የብዝሀ ቀበሌ መስፈርትን አሟልተዉ ከተገኙ በዚህ ደንብ መሰረት ወደ ብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት እንዲያድጉ ይደረጋል።

፪. አንድ የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበርና አገልግሎት ሰጪ ድርጅት የተመሰረተበት አስተዳደራዊ እርከን ወደ ከተማ ማዕረግ ካደገ እና በከተሞች ዉሃ አገልግሎቶች ደረጃ ፍረጃ መመሪያ መሰረት የከተማ ውኃ አገልግሎት ድርጅት ደረጃን አሟልቶ ከተገኘ ወደ ከተማ ውሃ አገልግሎት ድርጅትነት ሊያሳድግ ይችላል።

20. Grade Change of Association and Service Provider Organization

1. If association and federation fulfill the multi-kebele requirements, they shall be upgraded to the level of a multi-kebele service provider organization.

2. An association and service provider organization may be upgraded to an urban water service organization if the administrative level at which it is established is promoted to the rank of a town and if it meets a grade of an urban water service organization as prescribed by the urban water services classification guidelines.

ክፍል አራት ፥ የገጠር መጠጥ ውሀና ሣኒቴሽን ማህበራት ፌዴሬሽን ሃላፊነት እና አደረጃጀት

Part Four : Federation’s Responsibilities and Structure

፳፩. የገጠር መጠጥ ውሀና ሣኒቴሽን ማህበራት ፌዴሬሽን የሚከተሉት አቋም ይኖሩታል፡-

፩. የፌዴሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ፣

፪. የፌደሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ፣

፫. እንደ አስፈላጊነቱ ማበረታቻ የሚከፈላቸዉ የሰለጠኑ ብቁ የውሃ ጠጋኝ ባለሞያዎች ይኖረዋል

21. Federation shall have following Structure

1. General Assembly;

2. Executive committee;

3. A trained and competent water schemes maintenance technician who is provided with incentives, as needed.

፳፪. ስለ ማህበራትና ማህበራት ፌዴሬሽን ጠቅላላ ጉባዔ ስልጣንና ተግባር

፩. ጠቅላላ ጉባዔ የማህበራትን ሥራ አስፈጻሚ አባላትን በሙሉ ያቀፈ ሆኖ የማህበራት ፌዴሬሽኑ የበላይ የሥልጣን አካል ነው።

፪. በወረዳዉ ተዘጋጅቶ በፌዴሬሽኑ የቀረበውን የመጠጥ ውሀ አገልግሎት ታሪፍ ይወስናል።

፫. የማህበራት ፌዴሬሽኑን አጠቃላይ እንቅስቃሴ እየገመገመ ውሣኔዎችን ያስተላልፋል፤የሥራ እቅድና በጀት ያፀድቃል።

፬. የማህበራት ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚዎችንና ንዑሳን ኮሚቴዎችን ይመርጣል፣ ከኃላፊነትም ያነሣል።

፭. እንደ አስፈላጊነቱ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎችንና ጥቅማ ጥቅሞችን ይወስናል።

፮. የማህበራት ፌዴሬሽኑን ሕልውና የሚመለከቱ ሌሎች ተግባራትና ኃላፊነቶች በመመሪያ የሚዘረዘሩ ይሆናል።

፯. ጠቅላላ ጉባኤው በአመት ቢያንስ ሁለት ጊዜ ስብሰባ ያደረጋል። ሆኖም ግን ልዩ ስብሰባ እንዲጠራ የሚያስገድዱ ሁኔታዎች ሲፈጠሩ በሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጥያቄ ወይም ከአባላቱ መካከል አንድ አራተኛው (1/4) አባላት ጥያቄ ሲያቀርቡ የጠቅላላ ጉባኤ ልዩ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል።

22. Powers and Responsibilities of General Assembly of Federation

1. Federation’s General Assembly consists of all executive member’s associations and it is the higher organ of the federation.

2. Endorses the tariff of potable water services set by the woreda.

3. Evaluates and decides on the activities of the federation; approves work plans and budgets.

4. Elects members of the executive committee and subcommittees of the federation and dismisses them.

5. Decides on various incentives and benefits, when necessary.

6. Other responsibilities and duties related to the existence/continuation of the federation shall be specified by a directive.

7. The General Assembly convenes at least twice in a year; however, it may conduct extraordinary meetings upon the request by the executive committee or by one-fourth of its members, when circumstances dictate.

፳፫. የማህበራት ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አመራረጥ

፩. በጠቅላላ ጉባዔው አብላጫ ድምፅ ይመረጣሉ። ፪. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ቁጥር ብዛት በመመሪያ ይወሰናል።

፫. የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የስራ ዘመን ከ 3 ዓመት መብለጥ የለበትም። የስራ ዘመኑን የጨረሰው የስራ አስፈፃሚው ኮሚቴን ለመተካት በሚደረግ ምርጫ ላይ የነባሩ ኮሚቴ አባል የሆነ በጠቅላላ ጉባኤው አባላት ጥንካሬው ከታመነበት ለአንድ ጊዜ በተጨማሪነት ለመጨረሻ ጊዜ ሊመረጥ ይችላል።

፬. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 የተቀመጠው የሥራ ዘመን እንደተጠበቀ ሆኖ ነገር ግን በዲሲፕሊን እና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከዚህ ያነሰ እንዲሆን በመመሪያ መወሰን ይቻላል።

፭. የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት በጠቅላላ ጉባኤ በማህበረሰቡ የተመረጡ ፈቃደኞች ናቸዉ። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

23. Election of Members of the Executive Committee of Federation

1. Members of the executive committee shall be elected by the majority vote of the General Assembly;

2. Number of the executive committee members shall be determined by a directive.

3. The term of office of the executive committee shall not exceed 3 years. However, a member may be re-elected if his performance is confirmed by the General Assembly of the federation.

4. Notwithstanding the term of office set forth in Sub-Article 3 of this Article, for disciplinary or other related reasons, it may be determined by a directive to reduce the term of office of committee members.

5. The executive committee members are elected by the General Assembly and the community and serve on voluntary basis።Particulars shall be determined by a directive.

፳፬. የማህበራት ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስልጣንና ተግባር

የማህበራት ፌዴሬሽን ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

፩. የማህበራት ፌዴሬሽኑን ጽ/ቤት ያደራጃል፣

፪. የራሱ ሰብሳቢ፣ም/ሰብሳቢ እና ፀሀፊ ይመርጣል

፫. የጠቅላላ ጉባዔውን ውሣኔ ይፈፅማል፣ያስፈጽማል፣

፬. የማህበራት ፌዴሬሽኑን በጀት ያንቀሣቅሳል፣

፭. የማህበራት ፌዴሬሽኑን አስፈላጊ የሆኑ ተግባራትን ያከናውናል፣

፮. አስፈላጊ በማበረታቻ ክፍያ አገልገሎት የሚሰጡ ሠራተኞችን ያሰማራል፣ ይቀጥራል፣

፯. የማህበሩ አባላትን ተራ በተራ ያሠራል፣

፰. የማህበራት ፌዴሬሽኑን ንብረቶች በጠቅላላ በአግባቡ እንዲያዙ ያደርጋል፣

፱. የማህበራት ፌዴሬሽኑን በመወከል ይከሳል፣ይከሰሳል፣

፲. የማህበራት ፌዴሬሽኑን በመወከል ከሦስተኛ ወገኖች ጋር ውል ይዋዋላል፣

፲፩. አመታዊ ሪፖርት ለጠቅላላ ጉባኤ እና ለሚመለከታቸው አካላት ያቀርባል፣የሚሰጠዉንም አቅጣጫ ይቀበላል ይፈጽማል፣

፲፪. የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች የማህበራት ፌዴሬሽኑ ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በግልና በጋራ ኃላፊነት የመውሰድ ግዴታ ይኖርባቸዋል፣

፲፫. በመመሪያ እና በመተዳደሪያ ደንብ የሚዘረዘሩ ኃላፊነቶች ይኖሩታል።

24. Powers and Responsibilities of the Executive Committee of Federation

The executive committee of federation shall have the following powers and functions:

1. Organizes the office of the federation.

2. Elects its Chairperson, Deputy Chairperson and Secretary;

3. Implements decisions of the General Assembly and causes their implementation;

4. Transacts the budget of the federation;

5. Carries out the necessary activities of the federation;

6. Deploys and hires workers who provide services by offering incentives;

7. Assigns works to members on a rotational basis;

8. Ensures all the federation’s assets are properly managed;

9. Sues and be sued by representing the federation;

10. Represents the federation in contracts with third parties;

11. Submits annual report to the General Assembly and the concerned bodies; considers and implements the directions given;

12. The executive committee members shall be jointly and severally liable for any damage they cause to the federation;

13. Shall have other responsibilities that will be determined by a directive and a bylaw.

ክፍል አምስት ፥ ብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት አደረጃጀትና አሰራር

Part Five : Organization and Working System of Multi-Kebele

፳፭. ብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ድርጅት

በዚህ ደንብ አንቀጽ ሁለት ንዑስ አንቀጽ ፲፬ የተጠቀስዉ እንደተጠበቀ ሆኖ የብዝሀ ቀበሌ የመጠጥ ዉሀ አደረጃጀት በሚከተለዉ አኳኋን ወይም መስፈርት ይሆናል።

፩. የሚቋቋመው ብዝሀ ቀበሌ ሊደራጅ የሚችለው ተቋሙ ወሰን ተሻጋሪ ሲሆን፣ በገቢው መጠን፣በተጠቃሚው ህዝብዘ ብዛትና በሌሎች መሰል ጉዳዮች ይሆናል።

፪. የሚቋቋመው ብዝሀ ቀበሌ በክልሉ ውስጥ ባሉ የገጠር ህብረተሰብ በጋራ በሚጠቀሙት ብዝሀ ቀበሌ የመጠጥ ውሃ ተቋማት ላይ ብቻ ይሆናል።

፫. ብዝሀ ቀበሌው ተጠሪነቱ ለስራ አመራር ቦርድ ይሆናል።

፬. የብዝሀ ቀበሌው ድርጅት የሥራ አመራር ቦርድ ተጠሪነቱ እንደአግባብነቱ ለወረዳ ጽ/ቤት፣ለዞኑ መምሪያ እና ለቢሮው ይሆናል። ዝርዝሩ በመመሪያ የሚገለጽ ይሆናል።

፭. የብዝሀ ቀበሌ ጽ/ቤት ተቀማጭነቱ አብዛኛው ተጠቃሚ ህብረተሰብ በሚገኝበት አማካይ ቦታ ላይ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ሊኖሩት ይችላል።

፮. ብዝሀ ቀበሌውን በደረጃ በመፈረጅ የተለያየ መዋቅር እንዲኖረው የሚደረግ ሲሆን ደረጃውም የተጠቃሚውን ህዝብና ቀበሌ ብዛት፣ እንድሁም የሚያገናኛቸውን የወረዳና ዞን ብዛት መሰረት ተደርጎ የሚሰጥ ይሆናል። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

25. Organization of Multi-Kebele

Notwithstanding to the provisions of Artice 2 sub-article 14, organization of the multi-kebele potable water shall be according to the following criteria.

1. A multi-kebele can be established based on the size of the water scheme, the size of the revenue, the number of beneficiaries, and other similar issues.

2. A multi-kebele will be established only on multi-kebele water schemes that are used jointly by rural communities in the region.

3. The multi-kebele shall be accountable to the Board.

4. The Board of the multi-kebele shall be accountable to the Bureau. Particulars shall be determined by a directive.

5. The multi-kebele office shall be situated at a location that is relatively central for the majority of the beneficiary communities; it may have branch offices as needed.

6. The multi-kebele shall be divided into grades with different structures; and the grading shall be based on the number of beneficiaries and kebeles, and the number of woredas and zones that connect them. Particulars shall be determined by a guideline.

፳፮. የብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ደረጃ አሠጣጥ

፩. ብዝሀ ቀበሌ በተለያዩ ደረጃዎች የሚመደቡ ሲሆን የመጠጥ ውሃ የተጠቃሚውን ህዝብ ብዛት፣ የሚያገናኘውን የዞን፣ የወረዳ እና የቀበሌ ብዛትን መሠረት በማድረግ የሚመደብ ሲሆን ዝርዝር ደረጃ አሰጣጡ በመመሪያ ይወሰናል።

፪. በዚህ ደንብ አንቀፅ ፳፮ንዑስ አንቀፅ ፩ በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት ቢሮው ደረጃ የማሻሻልም ሆነ የመቀነስ ኃላፊነት የሚኖረው ይሆናል።ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

26. Grading Multi-Kebele Service Providing Organization

1. Multi-kebele is graded based on size of potable water user population, number of zones, woredas, and kebeles that the multi-kebele connects. Particulars regarding grading shall be determined by a directive.

2. The Bureau shall have the responsibility of upgrading or downgrading a multi-kebelein accordance with the requirements set forth in Article 26, Sub-Article 1 of this Regulation. Particulars shall be determined by a directive.

፳፯. ብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት የሚከተሉት አደረጃጀቶች ይኖሩታል

፩. የበላይ ጠባቂ

፪. ቦርድ

፫. ብዛታቸው እንደአስፈላጊነቱ የሚወሰን ተቀጣሪ ሰራተኞች ሆነዉ ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

27. Multi-Kebele Service Provider Organization Shall Have the Following Structure

1. Oversight body

2. Board

3. It shall have employees whose number is need-based. Particulars shall be determined by a directive.

፳፰. የበላይ ጠባቂ አሰያየም

የበላይ ጠባቂ እንደ አግባብነቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ወይም የክልሉ ቢሮ ኃላፊ ሆኖ በየደረጃው ያሉ የአስተዳደር ደረጃ ላይ የተቀመጡ ሌሎች መሪዎችን ያቀፈ ይሆናል። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል

28. Nomination of the Oversight Body The oversight body incorporates, based on conditions, Zone Administrator, or Head of the Region’s Bureau and other leaders who are assigned at various administration levels. Particulars shall be determined by a directive.

፳፱. የበላይ ጠባቂ ተግባር እና ሃላፊነት

፩. የብዝሃ ቀበሌን በበላይነት የሚመራ፣ የሚጠብቅ እና ከቦርድ አባላት ጋር በጋራ የሚሰራ ይሆናል፤

፪. የቦርድ አባላትን ቁጥርና ኃላፊነት ደረጃን ይወስናል

፫. የቦርድ አባላትን በበላይነት ይከታታተላል፤ ይቆጣጠራል፣ ይመራል፤

፬. ቦርዱ እና ብዝሀ ቀበሌው ተግባሩን በተቀመጠው ደንብ መሰረት መስራቱን ይከታተላል፤

፭. ከቦርድ አባላት አቅም በላይ የሆኑ ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ላይ ውሳኔ ይሰጣል።

29. Roles and Responsibilities of the Oversight Body

1. The oversight body is an organ with a responsibility of leading and supervising the multi-kebele and works with board members.

2. Determines on the number and responsibilities of members of the Board;

3. Supervises, controls, and directs board members;

4. Supervises that the board and multi-kebele have carried out their activities as per the law;

5. Makes decisions on socioeconomic and political issues that are beyond the capabilities of board members.

፴. የብዝሃ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት የቦርድ አባላት አደረጃጀት

፩. ቦርዱ በአስተዳደር እርከኑ የሚወከሉ አባላትን እና የማህበራት ተወካዮችን ሊያካትት ይችላል።

፪. የቦርድ አባላት ስብጥር አሰያየም እና ቁጥር በመመሪያው ይወሰናል።

፫. የማህበራት ተወካዮች የቦርዱ አባላት የሥራ ዘመን ሦስት ዓመት ይሆናል። ሆኖም ለመጨረሻ ጊዜ ሁለተኛ ዙር ሊሰየም ይችላል።

፬. የመንግስት መዋቅር የቦርድ አባላት የሆኑ እንደአስፈላጊነቱ አደረጃጀቱ የሚቀጥል ይሆናል።

፭. በዚህ ደንብ መሰረት የቦርዱ የስራ ዘመኑን ከማጠናቀቁ በፊት የቦርድ አባላት ኃላፊነታቸውን እና ግዴታቸውን በአግባቡ ባለመወጣታቸው ምክንያት ከኃላፊነት ሊነሱ ይችላሉ።

፮. የቦርድ አባላት በፈቃደኝነት በማህበረሰብ የተመረጡ ሲሆኑ ብዝሃ ቀበሌው እንደ አቅሙ በየስብሰባዉ ክፍያ ይኖረዋል።

30. Organization of Board Members of the Multi-Kebele Service Providing Organization

1. The board may incorporate members represented from the administrative levels and representatives of associations.

2. Composition, nomination, and number of board members shall be determined by a directive.

3. The term of office the board members who represent associations shall be three years. A board member may be re-elected for the second term for a final time.

4. Notwithstanding that members change periodically, Government structure shall have a permanent position in the Board;

5. Board members may be removed from office before the end of their term due to failure to properly discharge their responsibilities and duties as prescribed by this Regulation.

6. Board members are elected by the community and serve on voluntary basis; they shall not be remunerated by the multi-kebele.

፴፩. የብዝሃ ቀበሌ ቦርድ ኃላፊነትና ተግባር

፩. የብዝሀ ቀበሌውን በበላይነት ይመራል፤ ይቆጣጠራል፤

፪. የብዝሀ ቀበሌውን የግዢ፤ የፋይናንስ እና ንብረት ቁጥጥር ስርዓት ይዘረጋል፤ አፈፃፀሙንም ይከታተላል።

፫. የብዝሀ ቀበሌውን ፋይናንስ እና በጀት ማጽደቅ፣

፬. በቢሮው የተቀመጠውን ዝቅተኛ የንፁህ መጠጥ ውሃ አገልግሎት ታሪፍ መወሰን፣

፭. የብዝሃ ቀበሌ ሰራተኞችን መቅጠር፣ መገምገም እና ማሰናበት። ዝርዝሩ በመመሪያ ይገለጸል።

፮. የድርጅቱን መዋቅር ያጸድቃል፣ የሰራተኞችን የደመወዝ ስኬል ይወስናል ፣ አበል እና ጥቅማጥቅሞችን ያጸድቃል፣

፯. የተወሰነውን ሀላፊነት እና ስልጣኑን ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሊሰጥ ይችላል፣

፰. የብዝሃ ቀበሌ ድርጅትን በመወከል መክሰስ እና መከሰስ፣

፱. በብዝሃ ቀበሌው ላይ ለሚያደርሱት ጉዳት በጋራ እና በተናጠል በሕግ ተጠያቂ ይሆናሉ፣

፲. ሌሎች ተግባር እና ኃላፊነቶች በመመሪያው የሚገለጽ ይሆናል።

31. Responsibilities and Duties of the Board of the Multi-Kebele

1. Oversees and controls the multi-kebele;

2. Establishes the procurement, finance and property management system of the multi-kebele; follows up the implementation thereof;

3. Approves the finance and budget of the multi-kebele;

4. Decides on the potable water service tariff set by the Bureau;

5. Recruits, evaluates, and dismisses employees of the multi-kebele. Particulars shall be determined by a directive;

6. Approves the structure of the organization; defines salary scale of employees; approves their allowances and benefits;

7. May delegate some of its responsibilities and powers to the executive committee;

8. Sues and be sued representing the multi-kebele

9. Board members shall be jointly and severally liable for the losses they cause to the multi-kebele;

10. Its other duties and responsibilities shall be determined by a directive.

፴፪. የስራ አመራር ቦርድ የስብሰባ ስነስርዓት

፩. ቦርዱ እንደአስፈላጊነቱ የሚያደርገው አስቸኳይ ስብሰባ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በየሩብ ዓመቱ መደበኛ ስብሰባውን ያደርጋል።

፪. ከቦርዱ አባላት መካከል ሁለት ሶስተኛው ከተገኙ ምልዓተ ጉባኤ እንደተሟላ ይቆጠራል።

፫. ቦርዱ ውሳኔ የሚያስተላልፈው በስብሰባው በተገኙት አባላት ድምጽ ብልጫ ነው።

፬. ሆኖም የተሰጠው ድምጽ እኩል ለእኩል ሆኖ የተገኘ እንደሆነ፣ ሰብሳቢው የደገፈው ወገን የቦርዱ ውሳኔ ይሆናል።

32. Procedures of Board Meetings

1. The Board shall hold its regular meetings on a quarterly basis; however, it may conduct extraordinary meetings, as may be needed.

2. There shall be a quorum when two-thirds majority of Board members are present.

3. Decisions of the Board shall be passed by a majority vote of members present.

4. In case of a tie, the Chairperson shall have a casting vote.

፴፫. የብዝሃ ቀበሌ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ኃላፊነትና ተግባር

፩. የብዝሃ ቀበሌውን ጽ/ቤት ያደራጃል፣ ፪. ቦርዱን ውሳኔ ተግባራዊ ያደርጋል፣

፫. የብዝሃ ቀበሌ አደረጃጀትን ፋይናንስና በጀት ያስተዳድራል፣

፬. የብዝሃ ቀበሌው ሁሉም ተግባራት እየተከናወኑ መሆናቸውን ያረጋግጣል፣

፭. የብዝሃ ቀበሌውን ንብረቶች ያስተዳድራል፣

፮. ለቢሮው ሪፖርት እና ላልች አስፈሊጊ መረጃዎችን ያቀርባሌ፣

፯. በመመሪያው የሚዘረዘሩ ሌሎች ኃላፊነቶች ይኖሩታል።

33. Responsibilities and Duties of Manager of the Multi-Kebele

1. Shall organize office of the multi-kebele;

2. Implements the decisions of the Board;

3. Administers finance and budget of the multi-kebele structure;

4. Ensures that all activities of the multi-kebele are being carried out;

5. Manages assets of the multi-kebele;

6. Submits reports and other necessary information to the Bureau;

7. Shall have other responsibilities as specified by a directive.

፴፬. የብዝሀ-ቀበሌ ድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ ሥርዓት

የብዝሀ-ቀበሌ ድጋፍ፣ክትትልና ግምገማ ሥርዓት የቢሮው እና የበላይ ጠባቂ ኃላፊነት ነው።

34. Support, Monitor, and Evaluation of Multi-Kebele

Support, supervision, and evaluation of the multi-kebele is responsibility of the Bureau and the oversight body.

፴፭. የሰው ኃይል አደረጃጀት

ብዝሀ ቀበሌ እንደየደረጃው የተለያየ የሰው ኃይል መዋቅር የሚኖረው ሲሆን የሰራተኞች የስራ መደብ በቋሚነትና በኮንትራት ቅጥሩን እንደየስራው ክብደት እና በድርጅቱ አቅም በሁሉም ደረጃ ብዝሀ ቀበሌ የሚሟላ ሆኖ ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

35. Human Resource Organization

A multi-level kebele has a various workforce structure based on its grade; and employees occupy positions on permanent and temporary bases depending on the workload and the capacity of the organization at all grades of the multi-kebele. Particulars shall be determined by a directive.

ክፍል ስድስት ፥ የገጠር የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት ምዝገባ እና መተዳደሪያ ደንብ

Part Six : Registration and Bylaw of Water Service Organization

፴፮. የገጠር የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት ስም፣ አድራሻና አርማ፡

፩. ማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት ማህበር፣የማህበራት ፌዴሬሽን ወይም ብዝሃ ቀበሌ የራሱ የሆነ መጠሪያ ስምና ምልክት /አርማ/ ሊኖረው ይገባል።

፪. ከማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት ስም ቀጥሎ “……የገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበር “………. የቀበሌ ገጠር መጠጥ ውሀና ሳኒቴሽን ማህበራት ፌዴሬሽን” ወይም “……….ብዝሀ ቀበሌ የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ድርጅት ” የሚል ቃላት መፃፍ ይኖርባቸዋል።

፫. የውሃ አገልግሎት ድርጅቱ የራሱ አድራሻ ሊኖረው ይገባል።

36. Name, Address, and Logo of Water Service Organization

1. Any water service organization’s association, federation or multi-kebele shall have its own name and logo.

2. Next to the name of any water service organization, an expression “…. Rural Potable Water and Sanitation Association”, “…. Kebele Rural Potable Water and Sanitation Associations’ Federation” or “…. Multi-kebele Rural Potable Water and Sanitation Organization” shall follow;

3. The water service organization shall have an address.

፴፯. ገጠር የመጠጥ ውሃ እና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት ምዝገባ፡-

፩. ማንኛውም በዚህ ደንብ መሠረት የሚቋቋም የውሃ አገልግሎት ድርጅት በቢሮው መመዝገብ ይኖርበታል።

፪. ምዝገባው የሚካሄደው ለመጠጥ ውሃ አገልግሎት ሰጪ እና በስሩ ላለው ማህበር በጋራ ነው።

፫. በቢሮው በኩል የሚደረገው ምዝገባ አግባብ ባለው የቢሮው መዋቅር ስር ሊሆን ይችላል። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

፬. ማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት እንደተቋቋመ የምዝገባ ማመልከቻውን ከሚከተሉት መረጃዎች ጋር አያይዞ ለመዝጋቢው አካል ያቀርባል።

ሀ) የመስራች ስብሰባ ቃለ ጉባኤ፣

ለ) የውሃ አገልግሎት ድርጅቱ መተዳደሪያ ደንብ፣

ሐ) የማህበሩ አባላት ስም ዝርዝር፣

መ) በስሩ ያሉት ማህበራት የሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት ስም፣ አድራሻና ፊርማ፣

ሠ) የፌዴሬሽን ወይም የቦርዱ ሥራ አመራር ኮሚቴ አባላት ስም አድራሻ እና ፊርማ

ረ) ይህን ደንብ ለማስፈፀም በሚወጡ መመሪያዎች መቅረብ ይኖርበታል።

፭. መዝጋቢው አካል መረጃዎቹ ተሟልተው ከቀረቡ በአጭር ጊዜ ወስጥ ለውሃ አገልግሎት ድርጅቱ የምስክር ወረቀት ይሰጣል።

፮. በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት የተሰጠ የምስክር ወረቀት የውሃ አገልግሎት ድርጅቱ በዚህ ደንብ መሠረት የተቋቋመ ለመሆኑ በቂ ማስረጃ ይሆናል።

፯. በቢሮው በኩል የሚደረገው ምዝገባ በየአንድ ዓመቱ ይታደሳል፣ ለእድሳት የሚያስፈልጉ ዝርዝር ሁኔታዎች በመመሪያ ይወሰናል።

፰. በክልሉ በሚመለከተው የመንግሥት ባለስልጣን የሚደረጉ ምዝገባዎችና እድሳት አግባብነት ባላቸው ሕጐች መሠረት ይከናወናል።

፱. ማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት ከተቋቋመበት ዓላማ ውጭ ሲንቀሳቀስ ከተገኘ በዚህ ደንብ መሠረት በቅርበት የሚመራው አካል የተፈቀደለትን ሥራ እንዳይሰራ አግባብ ባለው አካል ሊታገድ ይችላል።

፲. ይህ ደንብ ከመውጣቱ በፊት የተመሠረቱ የውሃ አገልግሎት ድርጅቶች በስልሣ ቀናት ውስጥ በዚህ ደንብ መሠረት ዳግም ምዝገባ ያደርጋሉ።

37. Registration of Water Service Organization

1. Any water service organization established according to this Regulation shall be registered by the Bureau.

2. The registration shall be done jointly for the water service organization and the association under it.

3. The registration may be made by the relevant organ within the structures of the Bureau. Particulars shall be determined by a directive.

4. Any water and sanitation service provider shall lodge registration application together with the following information.

a) Minutes of the establishment meeting;

b) The bylaw of the water service organization;

c) Names of members of the association;

d) Names, addresses, and signatures of the executive committee members of the associations under the organization.

e) Names, addresses, and signatures of members of the federation or board;

f) Directives to be issued to implement this Regulation.

5. The registering organ shall issue a certificate to the water service organization within short period of time when the latter submits complete information.

6. A certificate issued under sub-article 5 of this Article shall serve as sufficient evidence for the establishment of the water service organization, as per this Regulation.

7. Registration through the Bureau shall be renewed annually; detail requirements for renewal shall be issued by a directive.

8. Registrations and renewals done by the relevant authority of the Region shall be conducted pursuant to appropriate laws.

9. If any water service organization is found operating outside the objectives for which it is established, it may be suspended by the appropriate body from carrying out any activity.

10. Water service organizations established prior to the issuance of this Regulation shall be re-registered within sixty days.

፴፰. ሕጋዊ ሰውነትና ኃላፊነት

፩. ማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት በዚህ ደንብ መሠረት ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ የሕጋዊ ሰውነት መብት ይኖረዋል።

፪. ማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት ካላቸው ጠቅላላ ካፒታል ወይም ሀብት በላይ በዕዳ ተጠያቂ አይሆኑም።

፫. ማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት ከሌላ የውሃ አገልግሎት ድርጅት ጋር በትብብር የመስራት መብት አለው።

38. Legal Personality and Liability

1. Any water service organization shall have a legal personality from the date of its registration.

2. Any water service organization shall not be liable beyond its capital or assets.

3. Any water service organization shall have the right to work in cooperation with another water service organization.

፴፱. ስለ ገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት መተዳደሪያ ደንብ

፩. እያንዳንዱ የገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት የራሱ መተዳደሪያ ደንብ ይኖረዋል

፪. መተዳደሪያ በዚህ ደንብ ከተዘረዘሩት በተጨማሪ የገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት መብትና ግዴታዎች ይገልፃል።

፫. መተዳደሪያ ደንቡ የሚከተሉትን ነጥቦች ማካተት አለበት።

ሀ) የገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት ስምና አድራሻ፣

ለ) የገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት አስተዳደራዊ መዋቅር፣

ሐ) የገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት የሥራ አመራር አካላት ስልጣን፣ ኃላፊነት ተግባር

መ) ስለገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት ሥራ አስፈፃሚ አባላትና ሌሎች የሥራ ኃላፊዎች ስያሜና የሥራ ዘመን እንዲሁም ከኃላፊነት ስለሚታገዱበት ወይም ስለሚወገዱበት ሁኔታ፣

ሠ) ስለስብሰባ አጠራር ሥነ-ሥርዓትና ስለድምፅ አሰጣጥ፣

ረ) ልዩ ውሣኔና ምልዓተ ጉባዔ ውሣኔ ስለሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች፣

ሰ) ስለገንዘብ አሠባሰብና አስተዳደር እንዲሁም አያያዝና አጠቃቀም፣

ሸ) ስለ ገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት ሠራተኞች ስምሪት፣ የማበረታቻ ወይም የቅጥር ክፍያ አፈፃፀም፣

ቀ) መተዳደሪያ ደንብ ስለሚሻሻልበት ሁኔታ፣

በ) ይህን ደንብ የማይቃረን ሌሎች አግባብነት ያላቸው ተያያዥ ጉዳዮችን መያዝ ይኖርበታል።

፬. የገጠር መጠጥ ውሃ ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅት መተዳደሪያ ደንብ ሲሻሻል የተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ ለቢሮው ቀርቦ ከዚህ ደንብና መመሪያ ጋር የማይቃረን መሆኑ ሳይረጋገጥ አይጸድቅም። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል።

39. Bylaw of Water Service Organization

1. Each water service organization shall have its own bylaw.

2. In addition to the rights and duties of a water service organization issued in this Regulation, the bylaw shall stipulate other rights and duties.

3. The bylaws of the water service organization shall include the following.

a) Name and address of the organization;

b) Administrative structure of the organization

c) Powers, duties and activities of the executive organs of the organization;

d) Appointment and term of office of the executive members and other officials of the organization and the conditions of their suspension or removal from office;

e) The procedures for summoning meetings and voting;

f) Issues that require special decision and decisions by a quorum;

g) Collection, administration, and utilization of finance;

h) Conditions on deployment, incentives and salaries of workers of the organization;

i) Conditions for the amendment of the bylaw;

j) Other issues which do not contradict with the provisions of this Regulation may be included;

4. When the bylaw of the water service organization is amended, it shall not be approved without ensuring that it is not contradicting with this Regulation and a directive under it.

፵. የማህበራት ፌዴሬሽን እና ብዝሀ ቀበሌ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት መፍረስ

፩. አገልግሎት ሰጪ ድርጅት የሚፈርሰው አገልግሎት ተቀባይ ማህበር ከሌለው ከሌላ አገልግሎት ሰጪ ጋር በመዋሀዱ ይሆናል።

፪. የፈረሰ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ንብረት ከኦዲት በኋላ እና ለጠያቂዎች ከተከፈለ በኋላ ለቢሮው መተላለፍ ይኖርበታል ።

፫. አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በመፍረሱ ምክንያት ቢሮው የአገልግሎት ሰጪውን ሂሣብና ንብረት ለሌላ መሠል አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ያስረክባል።

፬. ቢሮው አገልግሎት ሰጪው አገልግሎቱ ከተቋረጠበት ቀን ጀምሮ ከአገልግሎት ሰጪ ድርጅትነት ይሰርዘዋል፤ ከተሰረዘበት ቀን ጀምሮ ህልውናውን ያጣል።

40. Dissolution of Federation and Multi-kebele Service Provider Organization

1. If a service provider organization does not have a service recipient association or when it merges with another service provider, it shall dissolve.

2. The assets of a dissolved service provider organization shall be transferred to the Bureau after audit and payments are made to claimants.

3. Upon dissolution of a service provider organization, the Bureau transfers the former’s accounts and assets to another similar organization.

4. The Bureau shall cancel the service provider organization from the date of termination of the service; the organization shall cease to exist from date of its cancellation.

ክፍል ሰባት ፥ ስለ የገንዘብ ምንጭ፣ የገቢ አጠቃቀም፣ ኦዲትና ኢንስፔክሽን

Part Seven : Finance Sources, Revenue Utilization, Audit, and Inspection

፵፩. ስለገጠር መጠጥ ውሃ አገልግሎት ድርጅቶች የገንዘብ ምንጭ

የውሃ አገልግሎት ድርጅቶች ገቢ ከዚህ በታች ከተዘረዘሩት ምንጮች ይሆናል፣

፩. ከአባላት መመዝገቢያና ልዩ ልዩ መዋጮ

፪. ከውሀ አገልግሎት ክፊያ ፣ቧንቧ ከማስቀጠልና ከሌሎች የተያያዙ ሥራዎች የሚገኝ ገቢ፣

፫. ከስጦታ፤ ከእርዳታ እና ከቅጣቶች

41. Sources of Revenue of the Water Service Organizations

The revenues of water service organizations shall be obtained from the following sources:

1. Membership registration fees and miscellaneous contributions;

2. Water service fees, revenues from pipe extension and other related activities;

3. Donations, aids, and fines.

፵፪. የመጠጥ ውሃ ታሪፍ አወሳሰንና ክፍያ

፩. በየአስተዳደር እርከኑ የሚገኙ የመጠጥ የውሃ ታሪፍን የመወሰን ኃላፊነት የዞኑ ሆኖ በሁለት ዞኖች መካከል ልዩነት ሲኖር በቢሮዉ ታሪፍን ይወስናል ።

፪. ታሪፉ በሚወሰንበት ጊዜ የሚከተሉትን ከግንዛቤ ማስገባት ይኖርበታል፡-

ሀ) የአካባቢውን ማህበረሰብ የመክፈል አቅም ያገናዘበ፣

ለ) የውሃ ተቋሙን አስተዳደራዊ ወጪ ለመሸፈን የሚያስችል እና ለሌሎች አስፈላጊ ስራዎች መቆጠብ የሚያስችል

ሐ) የተጋነነ ትርፍን መሠረት ያላደረገ መሆን አለበት።

መ) የተቋሙን አይነትና አገልግሎት አሰጣጥ ያገናዘበ መሆን አለበት፣

ሠ) የውሃ ታሪፉ መጠንም ለማህበር አባላትም ሆነ አባል ላልሆነ ተጠቃሚ ልዩነት አይደረግም።

፫. ከዚህ በላይ የተደነገገው ቢኖርም የገጠር ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በተወሰኑ ሁኔታዎች ያለክፍያ ውሃ ማግኘት ያለባቸውን የኀብረተሰብ ክፍል ለይቶ በመወሰን ያለክፍያ የመጠጥ ውሃ አገልግሎትን ሊሰጡ ይችላሉ።

42. Determination of Potable Water Tariff and Utility Fee

1. Zone shall have the responsibility to set potable water tariff for the administrative levels; where there is disparity between tariffs of two zones, the tariff shall be determined by the Bureau.

2. When determining tariff, the following shall be taken into consideration:

a) The paying capacity of the community of the area;

b) Covering the costs of administration and other necessary activities of the water scheme;

c) Not based on exaggerated profit;

d) Type of the water scheme and its service quality;

e) No differential treatment for association members and non-members on the amount of water tariff.

3. Notwithstanding the above provisions, a rural water and sanitation service provider organization may provide potable water services for free by identifying those persons who deserve free water service.

፵፫. ስለ ገቢ አጠቃቀም

የገጠር ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅት በዚህ ደንብ አንቀፅ ፵፩ መሠረት የሚያገኛቸው ገቢዎች ለሚከተሉት ዓላማዎች ይውላሉ።

፩. የውሀ ተቋማቱን የኦኘሬሽንና ጥገና ወጭዎችን፣የመልሶ ግንባታ ወይም የማስፋፋያ ሥራዎችን ለማከናወን፣

፪. 2 አገልግሎት ሰጪ ድርጅቱ በማበረታቻ ለሚያሰማራቸው ወይም ለሚቀጥራቸው ሠራተኞችና ባለሙያዎች ደመወዝ፣

፫. የሕዝብ መፀዳጃ አገልግሎቶችን ለማቅረብ፣

፬. በጠቅላላ ጉባዔ/ቦርድ በሚፀድቀው መሠረት ለመጠጥ ውሀና ሳኒቴሸን ሥራ ጋር ለተያያዙ ሌሎች የልማት ፍላጐቶች፣

፭. ለመልሶ ግንባታ እና ለማስፋፊያ ስራዎች ገንዘብ ለመቆጠብ ፮. ለውሃ አገልግሎት የተሰበሰበው ገንዘብ ከላይ ከተገለጹት ዓላማዎች ውጪ ለሌሎች ጉዳዮች ማዋል አይቻልም

43. Use of Revenue

The revenues generated by a rural water and sanitation service organization in accordance with Article 41 of this Regulation shall be used for the following purposes.

1. To cover the costs of operation, maintenance rehabilitation or expansion works;

2. To cover the costs of those who the organization deploys on the basis of incentive provision or payment of salaries for its employees and technicians;

3. To provide public toilet services;

4. To meet other development needs related to potable water and sanitation activities as approved by the General Assembly/Board;

5. To save money for future rehabilitation or expansion works;

6. The money collected for water services cannot be used for purposes other than the ones mentioned above.

፵፬. የገጠር ውሀና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅቶች በጀት ዓመት

የማንኛውም የውሃ አገልግሎት ድርጅት የበጀት ዓመት ከሐምሌ ፩ እስከ ሰኔ ፴ ቀን ይሆናል።

44. Fiscal Year of Service Organizations

The fiscal year of any rural water and sanitation service organization shall be from July 8 to July 7.

፵፭. ኦዲትና ኢንስፔክሽን

፩. የገጠር ውሃ አገልግሎት ሰጪ ድርጅት ኦዲት በስሩ ያሉትንም ማህበራት ኦዲት ያካትታል።

፪. ኦዲቱ የሚከናወነው በቢሮው ውክልና በተሰጣቸው ሠራተኞች ተቋማት ነው። ዝርዝሩ በመመሪያ ይወሰናል

፫. የማንኛውም አገልግሎት ሰጪ ድርጅት እና በስሩ ያሉት ማህበራት ሂሣብ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ የሂሣብ ዓመቱ በተጠናቀቀ በ፫ ወራት ውስጥ ይመረመራል።

፬. የኦዲት ሪፖርቱ ለቢሮው፣ ለገጠር ውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ሰጪ ድርጅቱ፣ ለጠቅላላ ጉባዔው/ ለቦርድ አባላት ይቀርባል።

፭. ቢሮው በማናቸውም ጊዜ የውሃ አገልግሎት ድርጅቶችን የሥራ አፈፃፀም ሠነዶችና የፋይናንስ አቋም በሚመለከት ድንገተኛ ኢንስፔክሽን ራሱ የሚያካሂድ ወይም በሌሎች በሚወክላቸው አካላት ማካሄድ ይችላል።

45. Audit and Inspection

1. The audit of a rural water provider organization includes the audit of associations under it.

2. The audit is carried out by personnel delegated by the Bureau. Particulars shall be determined by a directive.

3. The rural water provider and associations under it shall be audited at least once in a year within 3 months after end of a fiscal year.

4. The audit report shall be submitted to the Bureau, the service provider organization and the General Assembly/Board.

5. The Bureau may at any time conduct a surprise inspection of the performance documents and financial position of the associations by its experts or through delegated organs.

ክፍል ስምንት ፥ ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

Part Eight : Miscellaneous Provisions

፵፮. የቢሮው ኃላፊነት

፩. አግባብ ያላቸውን አካላት በማስተባበርና አስፈላጊውን የሙያ ድጋፍ በመስጠት ይህን ደንብ የማስፈፀም ኃላፊነት አለበት።

፪. በዚህ ደንብ የተቋቋሙ የውሃ አገልግሎት ድርጅቶችን አሠራርና አፈጻጸም ይከታተላል፣ ይቆጣጠራል፣ ይገመግማል።

፫. የትኛውም አካል ከቢሮው እውቅና ውጪ በዚህ ደንብ የተቋቋሙ የውሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅቶችን ማሻሻል ወይም ማፍረስ አይችልም።

፬. በየደረጃው ባሉ የቢሮው መዋቅሮች በተሰባሰቡና በየጊዜው በክትትልና ግምገማ የሚገኙ መረጃዎችን መሠረት በማድረግ አዳዲስ ሀሣቦች እንዲነደፍና ተግባራዊ እንዲሆኑ ያደርጋል።

፭. ለመጠጥ ውሀ አገልግሎት የሚከፈለውን ታሪፍ ክፍያ መጠን ያጠናል ፣ይወስናል።

፮. የውሀ ስራ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች በዚህ ደንብ ከተካተቱት አሰራር ውጪ እንዳይተገብሩ ያስገድዳል።

፯. የገጠር መጠጥ ዉሃና ሳኒቴሽን አገልግሎት ድርጅቶች በውሀ ጥናት፤ ግንባታ እና አስተዳደር ሂደቶች ዉስጥ ጉልህ ተሳትፎ እንዲኖራቸዉ ያደርጋል።

46. Responsibilities of the Bureau

1. Implementing this Regulation by coordinating and providing professional support to the relevant organs.

2. Monitoring, controlling, and evaluating the operation and performance of organizations established under this Directive.

3. No organ may change or dissolve service organizations established under this Regulation without the knowledge of the Bureau.

4. Developing new concepts and implementing them based on the information collected from various levels of the Bureau structure during monitoring and evaluation.

5. Studying and determining the tariff for potable water service.

6. Compelling nongovernmental organizations that operate water works not to implement procedures which are not included in this Regulation.

7. Making rural potable water and sanitation service organizations to participate and play conspicuous roles in the study, construction, and administration of waterworks.

፵፯. የተከለከሉ ተግባራት

፩. የዉሀ ተቋማት በልማት ሥራዎች ወይም በተለያየ ምክንያት የሚነሱ እና በጉዳት ካሳ የሚገኙ እንዲሁም በዉሀ እና ዉሀ ነክ የተሰበሰቡ ሀብቶች ከዉሀ ልማት ሥራ ዉጪ ለሌላ ዓላማ ማዋል ፍፁም የተከለከለ ነዉ።ዝርዝሩ በመመሪያ ይገለፃል።

፪. የገጠር መጠጥ ዉሀ አገልግሎት የዉሀ መገኛዎችን ለብክነት፣ብክለት እና ጉዳት የሚዳርጉ ማንኛዉም ተግባር ተከለከለ ነዉ።ዝርዝሩ በመመሪያ ይገለፃል።

47. Prohibited Activities

1. It is strictly prohibited to use the compensation payment obtained from removal of water schemes due to development projects or other reasons, and resources collected from water and water-related works, for purposes other than water development works. Particulars shall be determined by a directive.

2. Any activity that wastes, pollutes and causes damage to water sources is prohibited. Details shall be determined by a directive.

፵፰. የመተባበር ግዴታ

ማንኛውም ሰው ለዚህ ደንብ አፈፃፀም አግባብነት ካላቸው ባለስልጣናት ጋር የመተባበር ግዴታ አለበት።

48. Duty to Cooperate

Any person shall have the duty to cooperate with the relevant officials regarding the implementation of this Regulation.

፵፱. ስለቅጣት

ማንኛውም ሰው ይህን ደንብ ወይም ደንቡን ለማስፈፀም የወጡ መመሪያዎችን ጥሶ ሲገኝ አግባብ ባለው የወንጀል ሕግ መሠረት ይቀጣል።

49. Penalties

Any person who violates the provisions of this regulation or the directives thereof shall be punishable with the relevant provisions of the Criminal Code.

፶. ተፈፃሚነት ስለማይኖራቸው ሕጐች

ይህን ደንብ የሚቃረኑ ማናቸውም ደንቦች፣ መመሪያዎችና ልማዳዊ አሠራሮች በዚህ ደንብ የተሸፈኑ ጉዳዮችን በተመለከተ ተፈፃሚነት የላቸውም።

50. Inapplicable Laws

No regulation, directive, and practice shall, in so far as it is inconsistent with this Regulation, has effect with respect to matters provided for by this Regulation.

፶፩ መመሪያ የማውጣት ስልጣን

ቢሮው ይህንን ደንብ ለማስፈፀም የሚረዱ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል።

51. Power to Issue Directives

The Bureau may issue directives for the implementation of this Regulation.

፶፪. ደንቡ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ ደንብ ከዛሬ ጥር 25 ቀን ፳፻፲፰ ዓ/ም ጀምሮ የፀና ይሆናል።

52. Effective Date

This Regulation shall be effective from the 2nd of February 2026

ወላይታ ሶዶ

ጥር 25 ቀን ፳፻፲፰ዓ/ም

ጥላሁን ከበደ

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት

Wolayita Sodo

02/02/2026

Tilahun Kebede

Chief Executive of South Ethiopia Regional State

Although the Amharic version of the regulation is the final signed version, the English translation has not yet been approved.