Table of Contents
የጥገና ሥራ አደረጃጀት
Organisation of the Maintenance
1. ዓላማ እና አጠቃላይ ሁኔታ
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሁሉም ባለድርሻ አካላት ለውሃ አገልግሎት ክፍያ መዋጮ የተደረገው ርብርብ አመርቂ (በመላው ወረዳ 100% የሚጠጋ መዋጮ) ሲሆን የማይካድ ጥገና ለማድረግም ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል።
Objective and Rational
In recent years there have been huge efforts by all stakeholders toward fee contributions (nearly 100% in all Woreda) and towards visible maintenance.

እጅግ አመርቂ እና በቂ ጥገና በቁጫ ተከናውኗል
Highly visible and adequate maintenance carried out in Kucha
1.1 ያልተሟላ የመከላከል ጥገና
ጥቃቅን የሚመስሉ ነገር ግን እጅግ ጠቃሚ የሆኑ የመከላከል ጥገናዎች የሚባሉ ከዚህ በታች ያሉትን መጠቀስ ይቻላል ፡-
Incomplete preventive maintenance
There were however numerous gaps in important, and less visible, preventive maintenance:

ያልተሸፈነ ቧንቧ፣ ነገር ግን ትልቅ ግምት የማይሰጣው(በግራ ያለውን ስዕል ተመልከት) ሆኖ ቧንቧው በተቆረጠ ሰዓት መላ የውሃ ስርዓቱን ሙሉ በሙሉ አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያደርግ ነው(በስተቀኝ ያለውን ስዕል ተመልከት)
Uncovered pipe, which might not look critical (left), but which might render the entire system non-functional when it breaks (right)

በሮችን ቀለም አለመቀባት እንደ ትልቅ ችግር ተደርጎ አይወሰድም(በግራ በኩል ያለውን ስዕል ተመልከት) ነገር ግን ከጥቂት አመታት በኋላ ከፍሬሙ እንዲላቀቅ መንስኤ ይሆናል! (ቀኝ በኩል ያለውን ስዕል ተመልከት)
An unpainted door does not seem like a huge problem (left), but a few years down the line it will! (right)

የሚያንጠባጥብ፣ ያልተቀየረ የውሃ ፎሴት (በግራ) የሚከተሉትን ችግሮች ያስከትላል፡፡ (በቀኝ ያለውን ተመልከት)
1) ብዙ ውሃ ማባከን እና የውሃ ማጠራቀሚያውን ባዶ ማድረግ
2) የውሃ ቦኖውን ማበላሸት
3) ውሃ ለመቅዳት አስቸጋሪ ማድረግን ያስከትላል
A leaking, unchanged faucet (left) will lead to (right):
1) Wasting a lot of water and emptying the reservoir
2) Damaging the water point
3) Making it difficult to fetch water
1.2 መደበኛ እንክብካቤ ያለማድረግ
አንዳንድ ምንጮች እና የውሃ ቦኖዎች በቦኖ ኮሚቴዎች ጥሩ የሆነ እንክብካቤ ይደረግላቸዋል።
Default in periodic care
Some springs and water points are well cared for by the WP committee.

በግራ በኩል ያለው ቦኖ ከ15 አመታት በላይ አገልግሎት የሰጠ ሲሆን በቀኝ በኩል ያለው ግን ቅርብ ጊዜ የተሠራ ተቋም ነው፡፡ሁለቱም በማህበረሰባቸው በጥሩ ሁኔታ እንክብካቤ የተደረገላቸው ተቋማት ናቸው፡፡
ሆኖም ፣ እንክብካቤ የማይደረግላቸው ተቋማትም ጥቂት የሚባሉ አይደሉም፡፡
The WP on left is over 15 years old, the one on the right is more recent, and both are well cared for by their communities.
However, they are numerous instances where this is not the case:

ይህም የእንክብካቤ ጉድለት በምንጮች ላይ ይስተዋላል፡፡እንደሚታወቀው ምንጮች የውሃ ዋስትናና አለኝታ ስለሆኑ እንክብካቤ ሊደረግላቸው ይገባል፡፡.
It concerns springs, which must be kept with care, as they are at the head of the network and the most important to guarantee water potablilty.


ወይም ስዕሉ ከቃላት በላይ የሚናገርለት የውሃ ቦኖውን ተመልከት
Or Water Points, where the picture tells more than words
1.3 ትኩረት ለሙያዊ ጥገና
የውሃ ቦኖዎችን በፈቃደኝነት ከመጠገን ልምድ ሙሉ አቅምን በመጠቀም ወደ ሙያዊ ጥገና ወደ ሚደረግ ልምድ ማሸጋገር፤ እያንዳንዱን የኔትወርኩ አካላት ሙሉ በሙሉ አገልግሎት ሳያቋርጡ ለማቆየት ስትራቴጂውን እንደገና መወሰን እና ለሁሉም ተዋናዮች የሥራ ክፍፍል ማድረግን ይጠይቃል።
ይህ ስልት የአስተሳሰብ ለውጥን ያካትታል፤ ይህንን የአስተሳሰብ ለውጥ ለማጠናከር በነበሩ ችግሮች ላይ፣ የውሃ አገልግሎቱን ዘላቂነት ላይ ተግዳሮት በሚሆኑ እና ሁሉም ባለድርሻዎች የበለጠ ሙያቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ትኩረት መስጠት ያስፈልጋል።
የመንግስት ባለሞያዎች ትክክለኛ ስርዓቶችን በመከተል በተደራጀ መንገድ የበለጠ መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል።
የውሃ ተጠሪዎች ሙሉ የቧንቧ መስመሮችን ለመፈተሽ እና በሁሉም የውሃ ኔትዎርኮች ውስጥ ያሉ ችግሮችን መፍታት ስለሚኖርባቸው በርካታ ተጨማሪ ስራዎች ማከናወን ይጠብቃቸዋል፡፡ የውሃ ተጠሪ ማካካሻን በተመለከተ የአሰልጣኙ ሚና ቀድሞ ያለውን አስተሳሰብ መቀየር ሊሆን ይገባል፡፡ ውጤታማ ሥራ ተገቢ ማበረታቻ ሊታጀብ ያስፈልገዋል።
Toward Professional Maintenance
Shifting from a voluntary maintenance of water points to a professional exhaustive maintenance of every component of the networks requires a redefinition of the strategy and a significant workload increase for all actors.
This strategy includes changing mindset. To reinforce this change in mindset, it is necessary to focus on existing problems, the risks to the sustainability of the water service, and the need for all actors to become more professional.
Government experts will have to be involved further in a more organised way, following precise protocols.
Water Agents will have much more work as they will have to diagnose entire pipelines and tackle problems in the full networks. The role of the coach is also to change the mindset regarding Water Agent compensation: real work requires decent compensation.
2. ፍቺዎች፡-
በዚህ ሰነድ ውስጥ (ሌላ ቦታ ካልተገለጸ በስተቀር) የዞኑ ባለሞያ የዞ/ው/መ የተቋማት አስተዳደር ባለሞያ ሲሆን እና የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ የ የወ/ው/ጽ/ቤት የተቋማት አስተዳደር ባለሞያ ተብሎ ይጠራሉ፡፡
Definitions:
Throughout this document (if not otherwise specified), Zone expert refers to ZWD Scheme Administration Expert and WWO expert refers to WWO Scheme Administration Expert.
2.1 ፍተሻ
የውሃ ተቋማትን ችግር/እንከን መለየት፣የውሃ ተቋማትን ደህንነት ሁኔታ እና ሁለንተናዊ ቁመና ለመፈተሽ የተዘጋጀ ቼክሊስት በመጠቀም የተቋሙን ችግር/እንከን መለየትና ቅጹን(ቼክሊስቱን) መሙላት። ይህ የፍተሻ ሥራ የሚጠናቀቀው በየዓመቱ በጥቅምት ወር ሲሆን ለተቋሙ የሚያስፈልገውን(ለዘላቂና አስተማማኝ የውሃ አገልግሎት) የማስተካከያ ሥራ የሚታወቀው /የሚለየው ፍተሻውን መሠረት አድርጎ ነው፡፡
Diagnoses
Identify the network problems, based on a checklist and fill in the Diagnosis Checklist. The diagnosis of all WP is completed in Tikimnt and defines the corrective measures required.
ችግሮችን ለመለየት ጥሩ ነው።
መፍትሄዎችን ለመለየት ግን ጥሩ አይደለም
Its good to identify problems
BUT
Not good to identify solutions
2.2 የማስተካከያ ሥራዎች
በፍተሻው የተለዩ ችግሮች እንዲቀረፉ መከናወን የሚገባቸው ሥራዎች፣
Corrective measures
Measures that need to be conducted to solve the problem identified in the diagnosis.
የማስተካከያ ሥራዎች የሚከተሉት ሊሆኑ ይችላሉ-
- ቴክኒካል ይዘት ያለው ድርጊት ሊሆን ይችላል
ለምሳሌ ያልተቀበረ እና ያልተሸፈነ የቧንቧ መስመር ካለ ቧንቧ የተጋለጠበት ቦታ ላይ ካብ መገንባት እና አፈር ማልበስ * መደበኛ/ተደጋጋሚ እንክብካቤ፣ የተዘረጋውን ሥርዓት መፈተሽ እና ሥርዓቱን ማስተካከል ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ችግር፡የውሃ ቦኖውና አካባቢው በጣም ቆሽሾ ተገኝቷል፡፡ ማስተካከያ ሥራ የቦኖ ዕለታዊ ጽዳት ማድረግ
Corrective measures can be:
- a technical action to be taken
e.g. There is a pipe uncovered build a dry wall and backfill * or the need to re-organize the periodic care e.g. Water point is muddy Organisation of daily cleaning
2.3 መደበኛ እንክብካቤ ሥራዎች
የውሃ ተቋሙ እንከን አልባ አገልግሎት እንዲሰጥ አስፈላጊ የሆኑ እና አስቀድመው የታወቁ በመደበኛነት እና በተደጋጋሚ መከናውን የሚገባቸው ሥራዎች ናቸው (በየቀኑ፣በየሳምንቱ፣በየወሩ ወ.ዘ.ተ)።
Periodic Care
These are predictable actions that must be performed regularly (from daily to yearly) to keep the network in perfect order.

2.4 የመደበኛ እንክብካቤ ሥርዓት ሰንጠረዥ
ለእያንዳንዱ የመደበኛ እንክብካቤ ሥራ የማከናወን ኃላፊነት የተሰጣቸውን ግለሰቦች እንዲሁም እያንዳንዱ ሥራ ግዴታ መከናወን ያለበትን ድግግሞሽ በዝርዝር የሚገልጽ፣ የሚያስቀምጥ የአሠራር ሥርዓት ሠንጠረዥ ነው፡፡ይህ ሰንጠረዥ ለእያንዳንዱ የውሃ ተቋም ምንጭ እና የውሃ መቅጃ ቦኖ መዘጋጀት አለበት፡፡
Organisation of periodic care table
A table listing the persons responsible for each periodic care task and the frequency with which these tasks must be performed. This table must be created for each spring and WP and is written in the WUA Book.
2.5 የማስተካከያ ሥራዎች ውሳኔ ማሳወቅና ስምምነት
የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበራት ፌዴሬሽን በዓመታዊ የውሃ ተቋማት የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ሊፈጽም ያቀዳቸውን የማስተካከያ ሥራዎች ውሳኔዎች ዝርዝር ለወረዳ ውሃ ጽ/ቤት በጽሑፍ በማቅረብ ስምምነት መፈጸም አለበት፡፡ በጽሑፍ የሚቀርበው ዝርዝር የፌዴሬሽን ህጋዊ ማህተም እና የሰብሳቢው ወይም የተወካዩ ፊርማ ያረፈበት መሆን አለበት፡፡
Corrective measure resolution engagement
The federation must formally engage with the WWO by listing corrective measures they will address during the maintenance campaign.
2.6 የB የማስተካከያ ሥራዎች፡-
ማንኛውም የማስተካከያ ሥራ በውሃ ተጠቃሚ ማህበር፣በውሃ ተጠሪ ወይም በፌዴሬሽን አቅም መፈታት የሚችል ከሆነ የ”B” ማስተካከያ ሥራዎች ይባላል፡፡
ፌዴሬሽኖች በሥራቸው ያሉትን ሁሉንም የ “B” ማስተካከያ ሥረዎች በዓመቱ የጥገና ጊዜ ሠሌዳ ሳያልፍ የማከናወን እና የማጠናቀቅ ግዴታ አለባቸው፡፡እነዚህ የ “B” ማስተካከያ ሥራዎች “B” ወይም “C” ተብሎ በተሰየሙ የውሃ ቦኖ ውስጥ ሊገኙ ይችላሉ፡፡
አንድ የውሃ ቦኖ ቢያንስ አንድ “B” የማስተካከያ ሥራ ተብሎ የተለየ ሥራ በራሱ በቦኖ ሆነ ከፍ ብሎ ባለ መስመር ወይም ግንባታ ካለ ያ ቦኖ “B” ተብሎ ይሰየማል።
B Corrective measure:
A B corrective measure is one that can be solved by the Association, the Water Agent or the federation.
The federation must undertake to solve all B corrective measures during the maintenance campaign (these B correctives measures can be in a network with B and C WP). If a water point has at least one B corrective measure identified in both the WP itself and the upstream structures, it has a grade of B.
2.7 “C” ማስተካከያ ሥራዎች
አንድ የማስተካከያ ሥራ የ“C” ማስተካከያ ሥራ ተብሎ የሚሰየመው የማስተካከያ ሥራው ግዴታ የተመዘገበ የሥራ ተቋም ቀጥተኛ ተሳትፎ ግዴታ አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ ብቻ ነው፡፡
አንድ የውሃ ተቋም ቢያንስ አንድ “C” የማስተካከያ ሥራ ተብሎ የተለየ ሥራ በራሱ በቦኖ ሆነ ከፍ ባለ መስመር ወይም ግንባታ ካለ ያ ቦኖ “C” ቦኖ ተብሎ ይሰየማል፡፡
C corrective measure:
A C corrective measure is one that can be solved only with the direct involvement of registered contractors.
A water point with a least one C corrective measure either concerning the WP itself or its upstream network has a grade of C.
2.8 የጥገና መውደቅ
የጥገና መውደቅ ማለት በአንድ ፌዴሬሽን ውስጥ በጥቅምት ወር የ“B” ማስተካከያ ተብለው ከተለዩት ቢያንስ አንድ የማስተካከያ ሥራ እስከ ሚያዚያ 30 ድረስ ሳይጠናቀቅ ሲቀር ነው፡፡
Maintenance fail:
Maintenance fails means that at least one B corrective measure identified in Tikimnt in the entire federation has not been properly addressed by Myazyia 30.
የሚከተሉት ችግሮች፡-
- ያልተቀበረ የቧንቧ መስመር/በበቂ ሁኔታ በአፈር ያለተሸፈነ የቧንቧ መስመር
- ያልተቀበረ የፈሳሻ ማስወገጃ ቧንቧ
- ቀለም ያልተቀባ በር
- የሚያንጠባጥብ ወይም በአግባቡ የማይሰራ ፎሴት
እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ችግሮች በጥቅምት ፍተሻ ወቅት መለየት ያለባቸው እና የማስተካከያ ሥራዎች ሊታቀድ ይገባል። ከነዚህ ችግሮች አንዱ እንኳን ማስተካከያ ሥራ ሳይከናወን ሚያዚያ 30 ከደረሰ ፌዴሬሽኑ በጥገና ሥራ እንደወደቀ ይቆጠራል፡፡ያልተጠናቀቀ የጥገና ሥራ = የጥገና መውደቅ
The following problems:
- Pipeline uncovered
- Evacuation pipe uncovered
- Door unpainted
- Faucets leaking heavily
must be identified in Tikimnt diagnosis and a corrective measure must be defined to solve them (all B corrective measures). If any one of these problems is not solved by Myazyia 30, the federation will fail due to uncompleted maintenance = Maintenance fail.
2.9የሚሠራ የውሃ ተቋም
አንድ የውሃ ተቋም የሚሠራ ነው ሊባል የሚችለው ተቋሙ ንፅህናው የተረጋገጠ በቂ እና የማይቆራረጥ የውሃ አገልግሎት የሚያቀርብ ከሆነ ነው፡፡
ንፅህናው የተረጋገጠ ሊሆን የሚችለው ምንጩና የምንጩ ዙሪያ መሠረታዊ የመከላከያ እና የጥበቃ መሥፈርቶች የሚያሟላ እና ቦኖው ውሃ የሚሰጥ ሲሆን ነው፡፡
Functional Water point:
A water point is considered functional if it is providing reasonably clean water (spring must have at least some basic protection & minimal cover) and cover basic needs (maximum repeated interruption < 3 days).
If a WP does not provide water due to a problem that is reparable by a water agent (pipe break, simple clogging…), it is considered as functional WP.

ከላይ ያሉት ሁለቱም ተቋማ በጥሩ ሁኔታ ላይ ያሉ አይደሉም . ይሁን እንጂ ምንጩ መሰረታዊ አገልግሎት እየሰጠ ነው፡፡ (አንዴ የምንጩ ሽፋን በፌፌዴሬሽኑ ከተሰራ) ቦኖው ውሃ ሊሰጥ ይችላል፡፡
ስለዚህ ከላይ የተገለጹ ሁለቱም ተቋማት የሚሠሩ ተቋማት ሊባሉ የሚችሉት የውሃ ተጠቃሚዎች ከእነዚህ ተቋማት አመታዊ መዋጮ ማዋጣት ሲችል እና በዚህም መዋጮ ፌዴሬሽኑ በራሱ አቅም የማስተካከያ ሥራ መሥራት ሲችል ብቻ ነው፡፡
Both of the above structures are in poor state. However the spring is providing basic function and protection (once a cover is added, which the federation can do), and the WP is providing water.
Therefore both these structures must be considered functional, so users need to pay the yearly fee and federations need to implement every corrective measure in their power.

በተቃራኒው ደግሞ ከላይ የተጠቀሱ የውሃ ተቋማት የማይሠሩ ተቋማት ሊባሉ የሚችሉት
- ምንጩ የውሃ አገልግሎት የማይሰጥ እና የምንጩ ዙሪያም የመከላከያ እና የጥበቃ መሥፈርቶችን የማያሟላ ሲሆን
- ቦኖው ውሃ የማይሰጥ እና ጥገናውም ከፌዴሬሽን አቅም በላይ ሲሆን ነው፡፡
የዚህ መልሶ ግንባታ ሥራ እንደ አዲስ ግንባታ የሚታሰብ እና ትልቅም የሆነ እንቬስትመንት የሚፈልግ ስለሆነ በውድድር ውጤት መስፈርት መሠረት ፌዴሬሽኑ አሸናፊ ሆኖ ሲገኝ መልሶ ግንባታው ሊሠራ ይችላል፡፡
Both of the above structures are non-functional:
- The spring is not providing basic function nor protection
- The WP is not providing water and its repair is far beyond federation capacity.
These heavy rehabilitations are considered as new investments, the prioritisation of these investments are based on federation score.
2.10 የውሃ ተቋማት ደረጃ ፡
የውሃ ተቋማት ደረጃ የሚያመላክተው የተቋሙን የፍተሻ ውጤት እና የማስተካከያ ሥራውን አተገባበር የሚያመላክት ነው፡፡
ጥንቃቄ ፡- የውሃ ደረጃ በራሱ በቀጥታ ምን ዓይነት እርምጃ መወሰድ እንዳለበት ለማወቅ የሚረዳ አይደለም፡፡ ምን መደረግ እንዳለበት ለማወቅ የማስተካከያ እርምጃ አተገባበር ያስፈልጋል ፡፡
Grading:
A simple grade that reflects the diagnosis results and the implementation of the corrective measure.
Careful: a grade by itself does not help identify the exact action to be carried out. The corrective measure is needed to know what has to be done.
2.11 የውሃ ቦኖ ደረጃ “A”፡
የሚሠራ የውሃ ቦኖ ሆኖ
- በጥቅምት የፍተሻ ወቅት ምንም የማስተካከያ ሥራ የማያስፈልገው ቦኖ ነው።
በአብዛኛዎቹ ኔትውርኮች ላይ ተደጋጋሚ ጥገና ስለሚያስፈልግ በዚህ ቦኖ ደረጃ ያሉ ቦኖዎች አጠራጣሪ ስለሆኑ በሚገባ ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው፡፡
- ወይም እነዚህ ሁሉም ቦኖዎች ከጥር እስከ ሚያዚያ ባሉት ጊዜያት የማስተካከያ ሥራ የተሠራላቸው ተቋማት ሊሆኑ ይገባል።
Water Point A:
Functional water point with:
- no corrective measure identified during the Tikimnt diagnosis
HIGHLY SUSPICIOUS as recurrent maintenance is needed on most networks
- or a water point where all corrective measures have been solved (between Tir and Myazyia).
2.12 የውሃ ቦኖ ደረጃ “B”፡
የሚሠራ የውሃ ቦኖ ሆኖ በጥቅምት ፍተሻ ወቅት ቢያንስ አንድ የB ማስተካከያ ሥራ ያለው እና ምንም የጥገና ሥራ ያልተሠራለት ቦኖ ነው።
Water Point B:
Functional water point with a least one B corrective measure identified in the Tikimnt diagnosis and not yet resolved.
2.13 የውሃ ቦኖ ደረጃ “C”፡
በፍተሻ ወቅት ቢያንስ አንድ C የማስተካከያ ሥራ ያለው እና ጥገና ያልተደረገለት ቦኖ ነው፡፡
Water Point C:
Functional water point with at least one C corrective measure identified in the diagnosis: and not yet resolved.
2.14 የውሃ ቦኖ ደረጃ “D”፡
የማይሰራ የውሃ ቦኖ ነው፡፡
Water Point D:
Non-functional water point.
3. ካላንደር
Calandar
ከላይ ባለው የቀን መቁጠሪያ ውስጥ የተዘረዘሩት የእንቅስቃሴዎች ዘዴዎች በእነዚህ ሰነዶች ውስጥ ይገኛሉ-
The methodologies for the activities listed out in the calendar above can be found in these documents:
መሰረታዊ ፍተሻ፣ የማስተካከያ ሥራ እና ተሳትፎ
መደበኛ እንክብካቤ ዘዴ
የጥገና እቅድ ዘዴ
የጥገና ክትትል እና ድጋፍ
የፍተሻ ማረጋገጫ
የማስተካከያ ሥራ ማረጋገጫ
4. አስተሳሰብ ለውጥ መፍጠር እና ማሰልጠን
ዓላማው በቀጥታ ኃላፊነት ላለው ሰው (የውሃ ተጠሪው) እና ቀጥተኛ ደጋፊ / ተቆጣጣሪው (የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ) ከጥገና ጋር የተዛመዱ ተግባራትን በትክክል የመተግበር ቴክኒካል አቅም እና የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር ወደ አንድ የጋራ ዓላማ ( አስተሳሰብ ) ማምጣት ነው።
ቀዳሚ ዓላማው የውሃ አገልግሎትን ዘላቂነት ማረጋገጥ ሲሆን በቀጣይ የጥገና ወጪዎችን በመቀነስ በተቻለ መጠን የተሻለውን ጥገና በመደበኛነት ማከናወን ነው፡፡ ሁሉም የታቀዱ የፍተሻ እና የማረጋገጫ ሂደቶች ይህንን ዓላማ ለመደገፍ እንደ ዘዴ የሚያገለግሉ መሆን አለባቸው.
ባለድርሻ አካላት የፌዴሬሽኑን ውጤት ለመጨመር ብለው የኔትዎርክ ችግሮችን ችላ ብለው ካዩ ይህ ወደ ኔትወርክ ውድቀት ሊያመራ ይችላል። በአንፃሩ ባለድርሻ አካላት ሚናቸውን እንደ ተቆጣጣሪ እና እንከን ፈላጊዎች (ማለትም ድጋፍ ሳይሰጡ እስኪወድቁ ከጠበቁ) አድርገው ካዩ ለፌዴሬሽኖች አቅም ካለመፍጠራቸውም በተጨማሪ ተስፋ ሊያስቆርጡ ይችላሉ።
Coaching and creating mindset
The objective is to convey to the person directly responsible (the water agent) and their direct supporter/supervisor (the WWO expert) the technical capacity to properly implement activities related to maintenance, as well as a sense of ownership towards a common objective (mindset).
The primary objective is to ensure the sustainability of the water service while minimising future maintenance costs by carrying out the best possible maintenance on a regular basis. All proposed diagnosis and validation processes must be understood as means of supporting this objective.
If actors overlook network problems to increase the federation score, this could lead to network failure. Conversely, if actors see their role as validators only (i.e. failing the federation without providing support), they will not create capacity and will discourage federations.
ይህ በምስሉ ላይ የሚታየው ሸጥ እንዲሁ እንደዋዛ ቸል የሚባል ከሆነ በምንጭ ሳጥኑ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ልያስከትል ይችላል፡፡
This gully might not look important but if nothing is done it can lead to the destruction of the spring box downstream - as shown in the picture below.
የግንዛቤና የቴክኒክ ድጋፍ ለማድረግ የድጋፍ ሞጁሉ ሲዘጋጅ የቢሮ እና የመስክ ተግባራዊ ልምምዶችን ማካተት ይኖርበታል፡፡
To impart both technical capacity and mindset, the coaching modules will include office based coaching and field practice, to cover:
4.1 በቢሮ ውስጥ የሚሰጥ ስልጠና;
ሀ. በአንድ ዓላማ ላይ የጋራ የሆነ አቋም መያዝ (በተለይ የአስተሳሰብ ዝንፈትን በማስወገድ ላይ ማተኮር)- ለምሳሌ የተሳሳተ ዝንባሌ በማንሳት ማብራሪያ መስጠት
ለ. ስለጠቅለላው የሥራ ሂደት (የጊዜ ሰሌዳ) መገንዘብ እና በሂደቱም የደረስንበትን ደረጃ ማወቅ
ሐ. ስለሥራ ሂደቱ ማብራራት( የቲዎሬቲካል ቴክኒካል እውቀት) - ተግባራቱ ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር ተብራርቷል
ይጠንቀቁ ፡ በቢሮ ላይ የተመሰረተ ስልጠና በጭራሽ በቂ አይደለም! ሰዎች እንቅስቃሴውን በትክክል እንዲረዱ በተግባር ሰርቶ ማሳየት ሁል ጊዜ አስፈላጊ ነው።
Office based coaching:
- Sharing of objectives (with focus on the mindset) – example of improper activity can help explanation - Global understanding of the whole process (calendar) and where we are in the process - Description of the process (theoretical technical knowledge) – which is set out in the details of activities below
Careful: Office based coaching is never enough! A real life demonstration is always necessary for people to really understand the activity.

4.2 የመስክ ሥልጠና፡
ልክ የመስክ ደረጃ ፈፃሚዎች በመስክ እንደሚፈጽሙት፤ በመስክ ላይ ያለውን ሂደት በትክክል ይለማመዱ፣ አሰልጣኙ ሥልጠና የሚሰጠው የሚከተለውን ለማስተላለፍ ያለመ ሊሆን ይገባል።
- ተግባራዊ የቴክኒክ ችሎታዎች (ለምሳሌ፡ ተግዳሮቶችን ማየት መቻል) - ድርጅታዊ አካሄድ (ለምሳሌ፡ መፍትሄዎችን ለማግኘት በጋራ ማሰብ መቻል) - የቁርጠኝነት አስተሳሰብ (ለምሳሌ፡ ሙሉውን ሂደት መከተል)
ደጋፊ አስተሳሰብ (የበለጠ ልምድ ያላቸው ባለሞያተኞች ጀማሪዎች ተገቢውን አስተሳሰብ እስኪይዙ እና እስኪቀበሉ ድረስ አብረው በመሆን እና በማሰልጠን መደገፍ)
Field coaching:
Practice the process in the field, exactly as the field level implementers must carry it out. The trainer aims to impart the following:
- Practical technical capacities (ex: being able to see problems) - Organisational approach (ex: being able to brainstorm together to find solutions) - Commitment mindset (ex: follow the whole line)
Supportive mindset (more experienced officials are there to support juniors by accompanying and coaching until they have understood and adopted the proper mindset)

የመስክ ልምምዱ(ሰርቶ ማሳየት እና ሥልጠና) ምንም እንኳን ረጅም እና ብዙ ጊዜ የሚወስድ ቢሆንም አቋራጭ መንገድ መከተል አያስፈልግም፡፡ ዋናው አሰልጣኝ አቋራጭ መንገድ ከተጠቀመ፣ የመስክ ሠራተኞች የጥገና ፕሮቶኮሉን ለመጣስ ዕድል/ነፃነት ያገኛሉ፡፡ ⇒ አቋራጭ መንገድ መከተል ውጤቱ ዝቅተኛ ጥራት ደረጃ ያለው ጥገና ያስከትላል፡፡
Even if long and time consuming, do not take any shortcuts in the field coaching (demonstration and training). If the superior takes a shortcut, it is most likely that the field implementers will also take liberty with the protocol
⇒ shortcuts will lead to poor maintenance.

ለእያንዳንዱ ተግባር፣ ሥልጠናው መጀመር ያለበት በከፍተኛ ደረጃ ከሚያስተባብሩ አካላት በተዋረድ እስከ ፈጻሚዎች ድረስ ሊሆን ይገባል፡፡ሙሉው ቅደም ተከተል 4 ደረጃዎችን ይዟል።
- ደረጃ 1 (1 የቢሮ እና 1 የመስክ ክፍለ ጊዜ ለየዞኑ)
የ ክልሉ ግብረ ኃይል እና አርአያ ማስተባበሪያ
→ የ ዞን ግብረ ኃይል አስተባባሪ፣ የዞኑ ባለሞያ፣ የ አርአያ ዞን ባለሙያ
- ደረጃ 2 (1 የቢሮ እና 1 የመስክ ክፍለ ጊዜ ለየወረዳ)
የዞኑ ባለሞያ እና የ አርአያ ዞን ባለሙያ
→ ወረዳ ማኔጅመንት ቡድን፣ ሁሉም የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ እና የአርአያ ባለሞያ
- ደረጃ 3 (1 የመስክ ክፍለ ጊዜ በየወረዳው ባለሙያ)
የአርአያ ባለሞያ እያንዳንዱን የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ በመጀመሪያው የፌዴሬሽኑ ድጋፍ ወቅት በጋራ ይሠራል፡፡
- ደረጃ 4 (1 የቢሮ እና 1 የመስክ ክፍለ ጊዜ በየፌደሬሽኑ)
የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሙያ በመጀመሪያው የልምምድ ተግባራቸው የውሃ ተጠሪዎችን ይደግፋሉ
For each activity, the coaching must start from the coordination (Mindset Gatekeeper) down to the lower implementer, the complete sequence can involve 4 steps:
- Step 1 (1 Office and 1 Field Session per Zone)
RTF & ARIA Coordination
→ ZTF coordinator, Zone expert, ARIA Zone expert
- Step 2 (1 Office and 1 Field Session per Woreda)
Zone expert and ARIA Zone expert
→ WMT, all WWO expert and ARIA expert
- Step 3 (1 Field Session per Woreda Expert)
ARIA expert accompany each WWO expert in their first federation
- Step 4 (1 Office and 1 Field Session per Federation)
WWO expert support the Water Agents for their first activity