Table of Contents
ለዉሃ አቅርቦት ተቋም መሬት የማቅረብና የመጠቀም መብት የሚያጎናፅፍ ማዕቀፍ
መግቢያ
ይህ ማዕቀፍ ለውሃ አቅርቦት ግንባታ መሬት ማቅረብና መጠቀም የሚያስችሉ ሂደቶችን በመከተል ለግንባታ የሚውለዉ መሬት አስተማማኝና ዘለቄታዊነት እንዲኖረው የሚያረጋግጥ ነው
ማዕቀፉ ሲነደፍ ጠቃሚ የኢትዮጵያ ህጎችን፤ፍታዊ የሆኑ የህብረተሰብ መብቶችንና የአከባቢ ጥበቃን መሰረት አድርጎ ነው ፍታዊ የህብረተሰብ መብቶች ሲባል ማንም አከል ወይም ግለሰብ ጠቃሚ መተዳደሪያ ሀብቶች ላይ ምንም አይነት ገደብና ቅነሳ እንዳይኖር የሚያረጋግጥ ነው
የመሬት የመጠቀም መብት ለማስተላለፍ ሁለት ክስተቶች አሉ
1ኛ) የመሬት ባለይዞታነት ማስተላለፍ ባለይዞታነት
2ኛ) የመሬት ባለይዞታነት እንዳለ ሆኖ የመሬት የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ
የማስተላለፍ ሂደቱ ለተለያዩ የውሃ አቅርቦት ግንባታ/መዋቅር ክፍሎች ላይ ይሆናል
Framework for land access and right of use for water supply structures
Introduction
This framework sets out the procedures to be followed to ensure that access and right of use to land on which water supply construction is built is durably secured.
These are designed in accordance with relevant Ethiopian legislation, fair social rights and environmental protection. Fair social rights are defined as ensuring that no individual faces a restriction or reduction in access to important livelihood resources.
There are two scenarios for the transfer of land use right:
i) Transfer of land holding
ii) Transfer of land use right without change of land holder
The process is then presented for different components of wash supply structures.
ተቀባይ>ነት ያለው የኢትዮጵያ ህግና ትርጉም
ይህ ማዕቀፍ የሚከተሉትን ተዓማኒ>ህጎችን ያጣቅሳል
- አዋጅ ቁጥር 1161/2011 ዓ.ም :ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት ፤ ካሳ የሚከፈልበት ፡እና ተነሽዎች መልሰው የሚቋቋሙበት
- አዋጅ ቁጥር 110/1999 ዓ.ም: የደቡብ ብሔሮች ፡ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል መንግስት የገጠር መሬት አስተዳደርና አጠቃቀም አዋጅ
- ደንብ ቁጥር 135/1999 ዓ.ም: ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በሚለቀቅ መሬት ላይ ለሰፈረ ንብረት ስለሚከፈል ካሳ የወጣ የሚንስትሮች ምክር ቤት ደንብ
- ደንብ ቁጥር 197/1992 ዓ.ም : የኢትዮጵያ የውሃ ሀብት አስተዳደር አዋጅ
- ደንብ ቁጥር 102/2004 ዓ.ም: የገጠር መጠጥ ውሃና ሳኒተሽን ማህበራት ማቋቋሚያ ደንብ
ትርጓሜ፡
- ውማ፡ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር
- ውማፌ፡ ውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር ፌደሬሽን
- ወውጽ/ቤት፡ ወረዳ ውሃ ጽህፈት ቤት
Applicable Ethiopian regulations and definitions
This framework refers to the following applicable regulations:
- Proclamation No.1161/2019: “Expropriation of Land holdings for public purposes, payments of compensation and resettlement of displace people”
- Proclamation No.110/2007: “The Southern Nations, Nationalities and Peoples Regional state Rural Land Administration and Utilization Proclamation”
- Regulation No.135/2007: “Council of Ministers Regulation on the Payment of Compensation for Property situated on landholdings expropriated for public purposes”
- Regulation No.197/2000: “Ethiopian Water Resources Management Proclamation”
- Regulation No.102/2012: “Rural Potable Water and Sanitation Association Establishment Regulation”
Definitions:
- WUA: Water User Association
- WUAF: Water User Association Federation
- WWO: Woreda Water Office
የመሬት የመጠቀም መብትን የማስተላለፊያ ሂደቶች
3.1 የውሃ ሃብት ባለቤትነት
3.1.1. አንቀጽ 5 ደንብ ቁጥር 197/1992 ዓ/ም እንደተደነገገው ሁሉም የሀገሪቱ የውሃ ሀብት የመንግስትና የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ሀብት ነው።
3.1.2 ለቤት ውስጥ ግልጋሎት የሚውል ውሃ ለሌላ ለማናቸውም ግልጋሎት ከሚውል ውሃ ቀደምትነት ይኖረዋል።(አንቀጽ 7.1 ደንብ ቁጥር 197/1992)
3.1.3 የውሃ ሀብቱ አስቀድሞ ለተወሰነ አገልግሎት በመዋሉ ብቻ ግልጋሎቱን ከሌሎች የውሃ ግልጋሎቶች ሁሉ ሊያስበልጠው ወይም የቅድሚያ መብት ሊያሰጠው አይችልም።(አንቀጽ 7.2 ደንብ ቁጥር 197/1992)
3.1.4 የምንጭን ውሃ ለውሃ አቅርቦት ስራዎች ከመጠቀም አውድ ሲታይ ማህበረሰቡ ህጋዊ የውሃው ባለቤት በመሆኑ የውሃዉ ያሁን ግልጋሎት ምንም ይሁን ምን ለቤት ዉስጥ ግልጋሎት ቅድሚያ በመስጠት ለመጠቀም የመወሰን መብት አለው፡፤
3.2 የመሬት ባለቤትነትን ማስተላለፍ
3.2.1 እንደ አዋጅ ቁጥር 1161 አንቀጽ 13 የተሻለው አማራጭ በ@አመክንዮ መሬትን መተካት አዋጭ እንደሆነ ነው
- ነባሩ የመሬቱ ባለቤት ተመጣጣኝ የመሬት ምትክ ይሰጠዋል
- እንደ ደንብ ቁጥር 135/1999 አንቀጽ 15 ተመጣጣኝ የመሬት ምትክ ትርጓሜ ለተመሳሳይ አገልግሎት የሚውል ምትክ መሬት ቢያንስ ለሰብል ምርት ምርታማ የሆነ መሬት በተቻለ መጠን ይሰጣል።
- በደንብ ቁጥር 135/1999 አንቀጽ 5 እና 6 በተቀመጠው ስሌት መሰረት ለአንድ ወቅት ምርት ካሳ ይከፈላል
3.2.2 በአዋጅ ቁጥር 11619 አንቀጽ 12 እንደተገለጸው የመሬት ምትክ መስጠት የማይቻል ከሆነ የገንዘብ ካሳ ይመቻችላቸዋል።
- የሚከፈለው ካሳ ሰብሉ ያስገኘው አማከይ አመታዊ ገቢ በ 10 ተባዝቶ የሚገኘው መጠን ይሆናል (ደንብ ቁጥር 135/1999 አንቀጽ 16.2)
-አማ?ካኝ የምርት ስሌት በደንብ ቁጥር 135/1999 አንቀጽ 13 በተቀመጠው ቀመር መሰረት ይሰላል።
3.2.3 መሬቱ የወል ከሆነ አንቀጽ 14 ተፈፂሚ ይሆናል።
3.3 መሬት በባለይዞታው ስር እንዳለ የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ
3.3.1 በአዋጅ ቁጥር 110/1999 ዓ.ም አንቀጽ 10.2 እንደተገለጸው የዉሃ መስመሮችና ሌሎች የመሰረተ ልማት አዉታሮች በሚዘረጉበት ወቅት በባለይዞታው መሬት ላይ የሚያልፉ ከሆነ ይህንኑ የመፍቀድ ግዴታ አለበት።
3.3.2 በአዋጅ ቁጥር 110/1999 ዓ.ም አንቀጽ 13.1 እንደተገለጸው መሬቱ ለህዝብ ግልጋሎት በጣም አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝና የአከባቢው ማህበረሰብ ሲወስን ባለይዞታው መሬቱን የመጠቀም መብቱን ሊያጣ ይችላል።
3.3.3 በደንብ ቁጥር 197/1992 ዓ.ም አንቀጽ 23.1 እንደተገለጸው የውሃ ስራዎችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ የንብረት አገልግሎቶች እና የመተላለፍ መብቶች በመሬት ባለይዞታዎች ላይ የግዴታ ይሆናሉ።
3.3.4 ከዉሃ አቅርቦት አዉታር አዉድ አኴያ ባለይዞታዉ ለውሃ መስመር ዝርጋታ፤ለውሃ አቅርቦት መሰረተ ልማት እና ለዉሃ ተጠቃሚዎች ወይም ለውሃ አገልግሎት አቅራቢዎች የመፍቀድ ግዴታ አለበት።
3.3.5 ባለይዞታው በዉሃ መሰረተ ልማት ምክንያት ነባር መረቱን የመጠቀም መብት የሚያጣ ከሆነ በደንብ ቁጥር 135/1999 ዓ.ም አንቀጽ 13 እና 16.2 በተገለጸው መሰረት የገንዘብ ካሳ መጠየቅ ይችላል።
Scenarios for the transfer of land use right
3.1 Water resource ownership
3.1.1 All the water resources of the country are the common property of the Ethiopian people and state, as set out in Article 5 of Regulation No.197/2000.
3.1.2 Domestic use shall have priority over and above any other water use (Article 7.1 of Regulation No.197/2000).
3.1.3 Pre-allocation of water resource shall not give it priority over and above any other use (Article 7.2 of Regulation No.197/2000).
3.1.4 In the context of the use of spring water for water supply works, it means that the community (representing the people) has legal ownership of the water and therefore has the right to decide the usage of this water, prioritising domestic use, regardless of the current actual usage.
3.2 Transfer of land holding right
3.2.1 If reasonably feasible, the preferred option is land substitution as per Article 13 of Proclamation No.1161;
- The existing holder of the land will be offered an equivalent substitute land.
- Equivalent substitute land is defined in Article 15 of Regulation No 135/2007 as “a plot of land capable of serving a similar purpose”, which is interpreted to mean as being at least as productive in terms of crop production.
- They will also receive compensation for one harvest, using the calculation mechanism as set out in Article 5 and 6 of Regulation No 135/2007.
3.2.2 If not possible, financial compensation will be arranged as referred to in Article 12 of Proclamation No.1161.
- The amount of financial compensation will be ten times the price of the average yield of crops obtained from the land (Article 16.2 of Regulation No.135/2007).
- The valuation of the average yield will be calculated using the formula set out in Article 13 of Regulation No.135/2007.
3.2.3 If the land is communal a landholding transfer to the WUA will be established and the Kebele chairman will represent the landholders
3.3 Transfer of land use right without change of landholder
3.3.1 The landholder is obliged to allow the construction of public network utility lines, such as water pipelines, to cross over his/her landholding, as per Article 10.2 of Proclamation No.110/2007.
3.3.2 Article 13.1 of Proclamation No.110/2007 states that any landholder may lose his/her land use right when the land is found to be more useful for public use, as determined by the local community.
3.3.3 The landholder is obliged to accept the transfer of the right of use (servitude) required for the implementation of water works, as per Article 23.1 of Regulation No.197/2000.
3.3.4 In the context of water supply networks, the landholder is obliged to allow the construction of pipelines and water supply infrastructure on his/her land, and to allow required right of use (such as the right of way) to water users or to water service providers.
3.3.5 In the event that the landholder loses his/her existing land use right because of water infrastructure, he/she is entitled to claim financial compensation as stated in Article 13 and 16.2 of Regulation No.135/2007.
ምንጭ፤የምንጭ ተፋሰስ ወይም ሌሎች የውሃ መገኛ አካላት
4.1 ትርጓሜ
4.1.1 የውስጠኛው የምንጭ ተፋሰስ ጥበቃ ወሰን ከምንም አይነት ብክለት እና ንክኪ ነፂ እንዲሆን መጠበቅ አለበት። ይህ ወሰን በጥብቅ ተከልሎ እና ታጥሮ ከተፈቀደላቸው ውሃ አገልግሎት ሰጪዎች ውጭ ማንም እንዳይገባ መደረግ ይኖርበታል። የሚመከረው ወሰን ክልል ከምንጩ አይን በላይ 5 ሜትር ሲሆን በፍፁም ከ 2 ሜትር ማነስ የለበትም።
4.1.2 የውጨኛው የምንጭ ተፋሰስ ጥበቃ ወሰን ከበካይ ነገሮች ለመጠበቅ ከፍተኛ ትኩረት መስጠትን ይሻል። በዚህኛው ክልል ሽንት ቤት መስራት፤የግብርና ኬሚካሎችን መጠቀም እንዲሁም ከፍተኛ ዉሃ የሚጠቀሙ እንደ ባህርዛፍ አይነት እፅዋቶችን መትከል በፍፁም አይፈቀድም። ሁሉም አይነት የውሃ ማፋሰሻ ግንባታወች መጠበቅ እና የውሀውን ፍሰት የሚያስቀይስ ምንም አይነት ለውጥ ማድረግ አይፈቀድም።የእፅዋት ሽፋኑም መጠበቅ ይኖርበታል። የሚመከረው ወሰን ክልል ከምንጩ አይን በላይ 50 ሜትር ሲሆን በፍፁም ከ 30 ሜትር ማነስ የለበትም።
4.1.3 የተፋሰሱአካባቢ የውሃ ፍሰቱ አጠቃላይ ወደ ምንጩ አይን የሆነውን በሙሉ ያካልላል፡ በተፋሰሱ አካባቢ የዉሃ ስርገትን ሊጨምሩ የሚችሉ ስራዎችን ለምሳሌ እንደ ዛፍ መትከል፤የአፈር እና የውሃ እቀባ የመሳሰሉ ስራዎችን መስራት ያስፈልጋል።
4.1.4 የምንጩ የክለላ ወሰን ግንባታ ከመጀመሩ አስቀድሞ በዉሃ መሀንዲሱ ይወሰናል።
Spring, spring catchment or other water sources
4.1 Definitions
4.1.1 The inner protection perimeter of the spring catchment is the area that is kept free of any contamination and tampering. This perimeter is strictly protected (fenced off) with no access other than authorised water service providers. The recommended radius of this perimeter above the spring is 5 metres, with an absolute minimum of 2 metres.
4.1.2 The outer protection perimeter of the spring catchment is the area in which strong attention is paid to potential contamination. Use of latrines, agricultural chemicals and plantations with high water requirements (e.g. eucalyptus) are forbidden. All water diverting structures must be preserved and no changes made to the intended water flow. All vegetative cover must be preserved. The recommended radius of this perimeter above the spring is 50 metres, with an absolute minimum of 30 metres.
4.1.3 The catchment area is the entire area which drains water towards the spring. Activities should be conducted to increase the water infiltration in this area, such as afforestation and soil and water conservation activities.
4.1.4 These perimeters will be determined by the water engineer prior to the start of construction.
4.2 አማራጮች
4.2.1 አማራጭ ሀ፡ ባለይዞታው ሁለቱንም የዉስጠኛ እና የውጨኛ ምንጭ ጥበቃ ወሰን ሲያስተላልፍ።ይህ ምርጡ አማራጭ ነው በጥሩ ሁኔታ ለረዥም ጊዜ ህጋዊ የመሬት የመጠቀም መብትን ያረጋግጣል።
4.2.2 አማራጭ ለ፡ ለዉስጠኛው ምንጭ ጥበቃ ወሰን ባለይዞታነቱን ሲያስተላልፍ እና ለውጨኛው ምንጭ ጥበቃ ወሰን የመሬት የመጠቀም መብቱን ሲያስተላልፍ።ባለይዞታው ለውጨኛው ምንጭ ጥበቃ ወሰን ባለይዞታነቱን ለማስተላለፍ አዋጭ ሆኖ ካልተገኝ የተሻለ አመራጭ ይሆናል። ይሁን እንጂ ይህ አማራጭ ከ 10 በላይ የውሃ ቦኖ ላለበት አውታር አያገለግልም።
4.2.3 አማራጭ ሐ፡ለዉስጠኛዉም ሆነ ለውጨኛው ምንጭ ጥበቃ ወሰን ምንም አይነት የባለይዞታነት ማስተላለፍ ሂደት የለለበት ነገር ግን የመሬት የመጠቀም መብት ብቻ ለሁለቱም ምንጭ ጥበቃ ወሰን ያለው።ይሁን እንጂ ይህ አማራጭ ከ 6 በላይ የውሃ ቦኖ ላለበት አውታር አያገለግልም።
4.3 የመሬት ባለይዞታነትን ማስተላለፍ
4.3.1 በደንብ ቁጥር 102/2004 ዓ.ም አንቀጽ 29.1 እንደተገለጸው የተገነቡ የመጠጥ ዉሃ አገልግሎት ተቋማት ለውሃ ተጠቃሚዎች ማህበራት የባለቤትነት መብት የሚተላለፍ ይሆናል።
4.3.2 ለባለ ግል ይዞታዎች ባለይዞታነት የሚተላለፈው በአነቀፅ 3.2.1 በተቀመጠው መሰረት ሲሆን የወል መሬት ከሆነ በክፍል 3.2.3 መሰረት ይሆናል።
4.3.3 ምንጩ ሙሉ በሙሉ በሚደርቅበት ጊዜ የውሃ ተጠቃሚዎች ማህበር ተለዋጭ መሬት የመጠየቅ መብት ይኖራቸዋል።
4.3.4 መካተት ያለባቸው ዶክሜንቶች
- በገጠር መሬት አስተዳደር የተዘጋጀ የባለቤትነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት (እዝል ለ ተመልከት) እንዲሁም Geo-referenced ካርታ (እዝል ሐ ተመልከት)
- በባለይዞታው እና ውማ የተፈራረሙበት የባለይዞታነት የማሰተላለፍ ስምምነት ሆኖ በቀበሌው ሊቀመንበር (የመንግስት ተወካይ)፤በቀበሌው ግብርና ሃላፊ< (የገጠር መሬት አስተዳደር ተወካይ)፤እና የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ተወካይ እውቅና ያለው።
4.4 መሬት በባለይዞታው ስር እንዳለ የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ
4.4.1 የመሬቱ ባለቤት እና የውማ የተፈራረሙበት የስምምነት ዶክሜንት (ዕዝል ሀ የአብነት ቅጽ ተመልከት) ሆኖ በቀበሌው ሊቀመንበር (የመንግስት ተወካይ)፤በቀበሌው ግብርና ሃላፊ< (የገጠር መሬት አስተዳደር ተወካይ)፤እና የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ተወካይ እውቅና ያለው።
4.4.2 በክፍል 4.1 እንደተገለፀው ስምምነቱ የሁለቱንም የምንጭ ጥበቃ ወሰን በተመለከተ መብት እና ግዴታቸውን ማብራራት ይኖርበታል።
4.4.3 ስምምነቱ ተፈፂሚ የሚሆነው ከተፈራረሙበት ቀን ጀምሮ ሲሆን የምንጩ ተፋሰስ መምከኑ ይፋ አስኪሆን ድረስ በሀይል ይቆያል።መምከኑን የመወሰን ወይም የማረጋገጥ ሀላፊነት የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ይሆናል።
4.2 Options
4.2.1 Case A: Landholding right transfer of both the inner and outer protection perimeter is the preferred option, as the best way to ensure proper land use in the long term.
4.2.2 Case B: Landholding right transfer of the inner protection perimeter, and transfer of land use right for the outer perimeter. This is the best alternative where the landholding right transfer of the outer protection perimeter is not feasible. However this option cannot be used for networks with more than ten water points.
4.2.3 Case C: No landholding right transfer is possible for either inner and outer protection perimeter, and so both perimeters have a transfer of land use right only. However, this option cannot be used for networks with more than six water points.
4.3 Transfer of landholding right
4.3.1 The landholding right of potable water schemes shall be transferred to the water user association responsible for the spring, as per Article 29.1. of Regulation No.102/2012.
4.3.2 The transfer of landholding right is completed as set out in clause 3.2.1. if the land is privately owned, and per clause 3.2.3. if the land is communal.
4.3.3 In the event that the spring dries completely, the water user association retains the right to propose an alternative use for the land.
4.3.4 The documments required include:
- landholding certificate (see example in Annex B), prepared by the Rural Land Administration, including a geo-referenced map, (see example in Annex C); and
- fandholding right transfer agreement, signed by the landholder and the WUA, endorsed by Kebele Chairman (representative of the state), the Kebele Agricultural Head (representative of the Rural Land Administration) and the WWO representative.
4.4 Transfer of land use right without change of landholdher
4.4.1 An agreement (see template in Annex A) will be signed between the landholder and the WUA, endorsed by the Kebele Chairman (representative of the state), the Kebele Agricultural Head (representative of the Rural Land Administration) and the WWO representative.
4.4.2 The agreement will define the rights and obligations relating to the two protection perimeters, as defined in section 4.1.
4.4.3 The agreement is effective from the date of signature and remains in force until the spring catchment is officially decommissioned. The WWO is responsible for the decision to decommission.
የውሃ ትቦ መስመር
5.1 ትርጓሜ
5.1.1 የውሃ ትቦ መስመር የሚያከትተው ሁሉንም የውሃ ትቦዎች እስከነ መከላከያቸው፤ማቋረጫዎች፤አየር ማስገቢያ፤እጣቢ ማስወገጃ፤እና የቫልብ ክፍሎችን።
5.1.2 የውሃ ትቦ መስመርን የመጠቀም መብት የውሃ አገልግሎት አቅራቢዎች ለመስመር ዝርጋታ እና ጥገና ያለገደብ ወደ ቦታው መድረስ እንዲችሉ የሚፈቅድ እና በቦኖ መስመሩ ላይ በዝርጋታ ወቅትም ሆነ ከተዘረጋ በኋላ ጉዳት እንዳይደርስ የመጠበቅ ሃላፊነትን ያካትታል።
5.2 መሬትን የመጠቀም መብት
5.2.1 መሬትን የመጠቀም መብት ማስተላለፍ (አገልጋይነት) የውዴታ ግዴታ እና ተጨማሪ ኮንትራት ተጠያቂነት ያለበት ነው (ያለ ስምምነት በህግ አስገዳጅ ሃላፊነት)። ይህ ተፈፂሚ የሚሆነው የውሃ ትቦ መስመሩ መዘርጋት ከጀመረበት ቀን ጀምሮ ይሆናል።
5.2.2 ጉዳት ወይም እንከን ሲገጥም ባለይዞታው ለውሃ ማህበራት ወይም በአቅራቢያው ለሚገኝ ውሃ አገልግሎት አቅራቢ ወዲያውኑ የማሳዎቅ ሃላፊነት አለበት።
5.2.3 ባለይዞታው በመስመር ዝርጋታ ምክንያት በሰብሉ ምርት ላይ ጉዳት ከደረሰበት በደንብ ቁጥር 135/1999 ዓ/ም አንቀጽ 13 እና 16.2 መሰረት የገንዘብ ካሳ መጠየቅ ይችላል።
Pipeline
5.1 Definitions
5.1.1 The pipeline includes all pipes and their protection, crossing structures, air vents, wash outs, and valve chambers.
5.1.2 The right of use for pipelines includes allowing unrestricted access for installation and maintenance to the water service providers, and a responsibility of care to avoid any damage to the pipeline, during and after installation.
5.2 Land use right
5.2.1 The transfer of the right of use (servitude) is a legal obligation and extra-contractual liability (legally binding responsibility without agreement). This is effective from the date of installation of the pipeline.
5.2.2 The landholder is responsible for reporting any instances of damage/defects to the WUA or nearest water service provider.
5.2.3 If the landholder incurs a loss of crop production directly related to the installation, he/she is entitled to claim financial compensation as stated in Article 13 and 16.2 of Regulation No.135/2007.
የዉሃ ቦኖ
6.1 ትርጓሜ
6.1.1 የውሃ ቦኖ ሲባል የሚያካትተው ቦኖ፤ልብስ ማጠቢያ፤ከብት ማጠጫ ገንዳ፤የእጣቢና የፍሳሽ ማስወገጃ ስርዓት እና እነዚህን መሰረተ ልማቶች የሚያገናኙ ሁሉንም የበንበ መስመሮች ይሆናል።
6.1.2 የውሃ ቦኖ የሚገነባበትን ቦታ(ከላይ ለተዘረዘሩት መሰረተ ልማቶች የተከፋፈለ መሬት) የመጠቀም መብት የሚከተሉትን ያካትታል።
- የውሃ አገልግሎት አቅራቢዎች ለመስመር ዝርጋታ እና ጥገና ያለ ገደብ ቦታው መድረስ ወይም መንቀሳቀስ እንዲችሉ።
- ውሃ ተጠቃሚዎች ቦኖው ጋ እና ልብስ ማጠቢያው ጋ ያለ ገደብ መድረስ ወይም መንቀሳቀስ እንዲችሉ።
- በቂ የከብት ማጠጫ ስፍራ እንዲኖር እና ያለ ገደብ ከብት ማጠጫው ገንዳ ጋ እንዲደርሱ
6.2 መሬት በባለይዞታው ስር እንዳለ የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ
6.2.1 የመሬቱ ባለቤት እና የውማ የተፈራረሙበት የስምምነት ዶክሜንት (ዕዝል ሀ የአብነት ቅጽ ተመልከት) ሆኖ በቀበሌው ሊቀመንበር (የመንግስት ተወካይ)፤በቀበሌው ግብርና ሃላፊ< (የገጠር መሬት አስተዳደር ተወካይ)፤እና የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ተወካይ እውቅና ያለው።
6.2.2 በክፍል 6.1.2 እንደተገለፀውስምምነቱ ስለ መሬት አጠቃቀሙ በተመለከተ መብት እና ግዴታቸውን ማብራራት ይኖርበታል።
6.2.3 ስምምነቱ ተፈፂሚ የሚሆነው ከተፈራረሙበት ቀን ጀምሮ ሲሆን መሰረተ ልማቶች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው< ይፋ አስኪሆን ድረስ በሀይል ይቆያል።አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውን የመወሰን ወይም የማረጋገጥ ሀላፊነት የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ይሆናል።
6.2.4 ባለይዞታው በመስመር ዝርጋታ ምክንያት በሰብሉ ምርት ላይ ጉዳት ከደረሰበት በደንብ ቁጥር 135/1999 ዓ/ም አንቀጽ 13 እና 16.2 መሰረት የገንዘብ ካሳ መጠየቅ ይችላል፡
Water points
6.1 Definitions
6.1.1 The water point includes the fountain (tapstand), wash table, cattle trough and washout or drainage system, and all pipelines connecting these infrastructures together.
6.1.2 The right of use for land on which the water point is built (delineated by the full area covered by the infrastructures mentioned above) includes allowing:
- unrestricted access for installation and maintenance to the water service providers;
- unrestricted access for the users to the fountain and wash table; and
- unrestricted and adequate access for livestock to the cattle trough.
6.2 Transfer of land use right without change of landholder
6.2.1 An agreement (see template in Annex A) will be signed between the landholder and the WUA, endorsed by the Kebele Chairman (representative of the state), the Kebele Agricultural Head (representative of the Rural Land Administration) and the WWO representative.
6.2.2 The agreement will define the rights and obligations relating to the land use as defined in clause 6.1.2.
6.2.3 The agreement is effective from the date of signature and remains in force until the infrastructure is officially decommissioned. The WWO is responsible for the decision to decommission.
6.2.4 If the landholder incurs a loss of crop production directly related to the installation, he/she is entitled to claim financial compensation as stated in Article 13 and 16.2 of Regulation No.135/2007.
ሌሎች የውሃ አቅርቦት መሰረተ ልማቶች
7.1 ትርጓሜ
7.1.1 ሌሎች የውሃ አቅርቦት መሰረተ ልማቶች የሚያካትቱት ከላይ ያልተካተቱትን ቋሚ መሰረተ ልማቶች ሲሆን ለምሳሌ እንደ የዉሀ ማጠራቀሚያ ገንዳ፤ማከፋፈያ ሳጥን የመሳሰሉትን ነው።
7.1.2 ሌሎች የውሃ አቅርቦት መሰረተ ልማቶች የሚገነቡበትን ቦታ (በመሰረተ ልማቱ ወይም በአጥር የተከለለ) የመጠቀም መብት የውሃ አገልግሎት አቅራቢዎች ለመስመር ዝርጋታ እና ጥገና ያለገደብ ወደ ቦታውመድረስ እንዲችሉ የሚፈቅድ እና በመሰረተ ልማቱ ላይ ጉዳት እንዳይደርስ የመጠበቅ ሃላፊነትን ያከትታል።
7.2 መሬት በባለይዞታው ስር እንዳለ የመጠቀም መብትን ማስተላለፍ
7.2.1 የመሬቱ ባለቤት እና የውማ የተፈራረሙበት የስምምነት ዶክሜንት (ዕዝል ሀ የአብነት ቅጽ ተመልከት) ሆኖ በቀበሌው ሊቀመንበር (የመንግስት ተወካይ)፤በቀበሌው ግብርና ሃላፊ< (የገጠር መሬት አስተዳደር ተወካይ)፤እና የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ተወካይ እውቅና ያለው።
7.2.2 በክፍል 7.1.2 እንደተገለፀውስምምነቱ ስለ መሬት አጠቃቀሙ በተመለከተ መብት እና ግዴታቸውን ማብራራት ይኖርበታል።
7.2.3 ስምምነቱ ተፈፂሚ የሚሆነው ከተፈራረሙበት ቀን ጀምሮ ሲሆን መሰረተ ልማቶች አገልግሎት መስጠት ማቆማቸው< ይፋ አስኪሆን ድረስ በሀይል ይቆያል።አገልግሎት የማይሰጡ መሆናቸውን የመወሰን ወይም የማረጋገጥ ሀላፊነት የወረዳው ውሃ ጽ/ቤት ይሆናል።
7.2.4 ባለይዞታው በመስመር ዝርጋታ ምክንያት በሰብሉ ምርት ላይ ጉዳት ከደረሰበት በደንብ ቁጥር 135/1999 ዓ/ም አንቀጽ 13 እና 16.2 መሰረት የገንዘብ ካሳ መጠየቅ ይችላል፡
Other water supply infrastructure
7.1 Definitions
7.1.1 Other water supply infrastructure includes all permanent infrastructure which are not classified in the sections above, for example reservoirs, distribution boxes etc.
7.1.2 The right of use for land on which other water supply infrastructure is built (delineated by a fenced area, or by the infrastructure itself) includes allowing unrestricted access for installation and maintenance to the water service providers, and a responsibility of care to avoid any damage to the infrastructure.
7.2 Transfer of land use right without change of landholder
7.2.1 An agreement (see template in Annex A) will be signed between the landholder and the WUA, endorsed by the Kebele Chairman (representative of the state), the Kebele Agricultural Head (representative of the Rural Land Administration) and the WWO representative.
7.2.2 The agreement will define the rights and obligations relating to the land use as defined in clause 7.1.2.
7.2.3 The agreement is effective from the date of signature and remains in force until the infrastructure is officially decommissioned. The WWO is responsible for the decision to decommission.
7.2.4 If the landholder incurs a loss of crop production directly related to the installation, he/she is entitled to claim financial compensation as stated in Article 13 and 16.2 of Regulation No.135/2007.
ዕዝል
የስምምነት አብነት ቅፅ
የመሬት ማረጋገጫ ማሳያ
ጅኦ ሪፈረንስድ ካርታ ማሳያ
Annexes
Agreement template
Land certificate example
Geo-referenced map example