SouthEthiopiaFlag
PROCEED
CentralEthiopiaFlag

Short Presentation of Diagnoses and Corrective Measure

ለፌዴሬሽን የተዘጋጀ ስለ ፍተሻ እና ማስተካከያ ሥራዎች ማብራሪያ

ይህ ሰነድ ስለፍተሻ ሂደት ደረጃዎችና ኅዳር ላይ ስለሚከናወነው ስለማስተካከያ ሥራዎች ልየታ የሚገልጽ ነው፡፡

ፍተሻ

  • ፍተሻ ማለት ቼክሊሰቱን በመጠቀም የኔትወርክ ችግሮችን መለየትና መመዝገብ ነው፡፡
  • የሁሉም ቦኖ ፍተሻ በጥቅምት ወር ይጠናቀቃል እንዲሁም ይህ ፍተሻም የማስተካከያ ሥራዎችን ለመለየት ይጠቅማል፡፡

ፍተሻ ችግሮችን ለመለየት ጥሩ ነው ነገር ግን መፍትሔዎችን አያመላክትም/አያሳይም፡፡

ኃላፊነት፡-ይህ ሥራ የሚሠራው በውሃ ተጠሪ እና በወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ ድጋፍ ነው፡፡

የማስተካከያ ሥራዎች

የማስተካከያ ሥራዎች የሚባሉት፡- ማስተካከያዎች ሆነው በፍተሻ ሠዓት የተለዩ ችግሮችን ለማስተካከል የሚተገበሩ ሥራዎች ናቸው፡፡ ማስተካከያ ሥራዎች ሊባሉ የሚችሉ፡-

  • የቴክኒካል ሥራዎች ሊሆኑ ይችላሉ

ያልተቀበረ/ያልተሸፈነ ቧንቧ ካለ = ካብ መካብ እና አፍር መመለስ

  • ወይም የመደበኛ እንክብካቤውን ሼል እንደገና ማደራጀት

ቦኖው ጭቃማ/በጭቃ የተበላሸ ከሆነ = ዕለታዊ የጽዳት ሥራ ማደራጀት

ኃላፊነት፡- በውሃ ተጠሪው በተለዩ ችግሮች መነሻነት የወ/ው/ጽ/ቤት ባለሞያ የማስተካከያ ሥራዎችን በፎርማቱን ይሞላል

የማስተካከያ ሥራዎችን እና ፍተሻውን እንዴት እንተግብረው

የኔትወርክ ፍተሻ ከውሃ ማህበራት ጋር በጋራ በመሆን የቧንቧ መስመሩን በመከተል እና በመፈተሽ እንዲሁም ሁሉንም የተቋማት ክፍሎችን በመፈተሽ ከምንጭ እስከ ቦኖ ድረስ መሆን አለበት፡፡
የቧንቧ መስመሩን ሳይፈትሹ የተቋሙን ዋና ክፍሎች ብቻ መፈተሽ እውነተኛ ፍተሻ ሊሆን አይችልም እንዲሁም ለኔትወርኩ ብልሽት ዋና ዋና ዋና የሚሆኑ ችግሮችን ለመለየት አያስችልም፡፡(ገላጣ የሆነ ቧንቧ፣መንገድ እና ገደል መሻገሪያዎችን)
ለምሳሌ፡- ምንጩ የተያዘበት ተፋሰስ አካባቢ የመከላከል ሥራ በተመለከተ:-ይህንን ጉዳይ ማወቅ የሚቻለው ከምንጩ ላይ በኩል/ራስጌ ሄዶ በማየት ብቻ ነው፡፡

  • በምንጩ ሳጥን ውስጥ ደለል ወይም ሼልሼር መኖር አለመኖሩ የሚታወቀው ሳጥኑን በመክፈት እና በማየት ብቻ ነው፡፡
  • የትርፍ ውሃ ማስወገጃ መደፈን አለመደፈኑ እና በጥሩ ሁኔታ መሆኑ የሚታወቀው ትርፍ ውሃው ወደ ሚወጣበት ጫፉ ጋር ድረስ ወርዶ በማየት ብቻ ነው፡፡

በፍተሻ መዝገቡ ላይ ያለውን የፍተሻ ቼክሊስት መስመር በመስመር የውሃ ተጠሪው ድምጹን ከፍ አድርጎ በሚያነብበት ጊዜ የውሃ ማህበራቱ በማድመጥ ችግሩን በአካል በመገኘት እና በማየት ይሳተፋሉ፡፡ ከውሃ ተጠሪው ጋር ቡድኑ ቼክሊስቱ ሲነበብ ምንም ችግር ያለመኖሩን ከተስማማ √ ያደርጋል. ነገር ግን ትንሽ ችግር ያለ እንደሆነ X ያደርጋል.

ችግር ያለው ከሆነ (X) የውሃ ተጠሪው ቡድኑን ተከታዩን ጥያቄዎች መጠየቅ ይኖርበታል:-

  • ይህ ችግር እንዲፈጠር ምክንያቱ ምንድነው? ይህ ችግር ዳግመኛ እንዳይፈጠር የሆነ አደረጃጀት መፍጠር እንችላለን? = መደበኛ የእንክብካቤ ማስተካከያ ሼል ለመሥራት
  • ይህንን ችግር ለማረም/ለመጠገን = ቴክኒካል የማሰተካከያ ሼል

የማስተካከያ ሥራው ስምምነትን ሕጋዊ ማድረግ

የውሃ ተጠሪው የወረዳ ማኔጅመንት ኮሚቴ(ወማኮ) በተገኙበት ለፌዴሬሽኑ የማስተካከያ ሥራዎችን በዝርዝር ማሳወቅ

ይህን ሰነድ በመፈረም ሁሉም አባላቱ ስለሚከተሉት ጉዳዮች ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል:

  • እነዚህ የተዘረዘሩ ጉዳዮች ለኔትወርኩ ጤናማነት እና ቀጣይነት ወሳኝ ስለሆኑ ትኩረት ሊሰጣቸው እንደሚገባ
  • የውማ፣የውማፌ እና የወ/ው/ጽ/ቤት የ B ማስተካከያ ስራዎችን በራሳቸው አቅም ሊሰሩ እንደሚገባ(ካልተሠራ ግን ፌዴሬሽኑ የሚወድቅ ይሆናል)
  • የውማ፣የውማፌ እና የወ/ው/ጽ/ቤት አንድ ወይም ከአንድ በላይ የC ማስተካከያ ሼል ሠርተው የውሃ አገልግሎቱን በቀበሌያቸው ማሻሻል እንደሚገባቸው(ይህን ከሠሩ አንድ ተጨማሪ ነጥብ በዳሽቦርድ ያገኛሉ)